አፋን ኦሮሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ነዉ



አፋን ኦሮሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ነዉ፡፡ ቋንቋዉ ከኦሮሚያ ክልል ዉጭ ባሉ ሌሎች ክልሎች በስፋት ይነገራል፡፡ በሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከሀረሪ ቋንቋ እኩል የክልሉ የስራ ቋንቋ ነዉ፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የስራ ቋንቋ ከመሆኑም ባሻገር የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ለአፋን ኦሮሞ በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ የአየር ጊዜ መድቦ ቋንቋዉ እንዲያድግ የህዝቦች ትስስር የበለጠ እንዲጎለብት ገንቢ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚጎራበቱ ሲዳማ፣ የም፣ካፋ፣ ቀቤና፣ ዳዉሮ፣ሀዲያ፣ ቡርጂ፣ ጌዲኦ፣ ኮንሶ ወዘተ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር በሚያደረጉት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች በአፋን ኦሮሞ ይግባባሉ፡፡ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላ፣ በትግራይ (ራያ አካባቢ)፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች ያሉ ህዝቦችም ቋንቋዉን በዕለት ተዕለት ኑሮአቸዉ በመግባቢያነት በስፋት ይጠቀማሉ፡፡ በፊንፊኔ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ከፊንፊኔ ልታገኝ የሚገባዉን ልዩ ጥቅም ለመዘርዘር በወጣዉ ረቂቅ አዋጅ ዉስጥ አፋን ኦሮሞ የከተማ መስተዳሩ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡ ቋንቋዉ ከኢትዮጵያ ዉጪም በጎሮቤት ሀገሮች በኬኒያ እና በሶማሊያ እና በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀሮች ጥቅም ላይ እንደሚዉል ይታወቃል፡፡
-
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስቱ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በራስ ቋንቋ የመጠቀም፣ ቋንቋ እና ባህላዊ ዕሴቶችን ለማሳደግ ያጎናጸፈዉን መብት በመጠቀም ቋንቋዉ እንዲያድግ፣ የስነ ጽሁፍ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቋንቋ እንዲሆን ሲሰራ ቆይቷል፣ አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ሂደት ባለፉት አመታት ቋንቋ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡ አፋን ኦሮሞ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚነገር ቋንቋ መሆኑ የቋንቋዉ ዕድገት የህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሮችን የበለጠ ያጠናክራል፡፡ ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችንንና የሀገራችን አንድነት የሚያጠናክር ሁነኛ መሳሪያ ሆኖም ያገለግላል፡፡
-
እንደ ሀገር የብዙ የስራ ቋንቋ መጠቀም የስልጣኔ እና ብዝሀነትን የማስተናገድ መገለጫ ነዉ፡፡ ለአብነትም በደቡብ አፍሪካ 11 የስራ ቋንቋዎች፣በኬኒያ 2፣በቤልጂየም 3፣ በፊንላንድ 2፣ በቡሩንዲ 3፣ በሩዋንዳ 4፣ በታንዛኒያ 2፣ በዑጋንዳ 2 የስራ ቋንቋዎች በሀገር ደረጃ የስራ ቋንቋ ሆነዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኦሮሞ ህዝብ አፋን ኦሮሞ የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዲሆን በተደጋጋሚ የሚያነሳዉን ጥያቄ ከግንዛቤ በማስገባት ፣ ቋንቋዉ የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

@መስፍን ተሾመ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa