በዚህ ዓመት የሚሰጠው 12ኛ ክፍል ላይ ብቻ ነው!

ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ታህሳስ 09/2012(TW)
የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በዚህ ዓመት የሚሰጠው 12ኛ ክፍል ላይ ብቻ ነው!
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ አስቀድሞ ቢነገርም አንዳንድ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን እያዘጋጁ መሆኑን መረጃ እየደረሰው ነው፡፡
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ለኢቲቪ እንደገለፁት ለአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ማድረግ እንደማይገባ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የክፍል ፈተና ብቻ እንደሚፈተኑ ለማስታወስ ለሁሉም ክልሎች ተቋሙ ድብዳቤ ፅፏል ብለዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ብሄራዊ ፈተና የሚወስደው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑን ተማሪዎችም ወላጆችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት እንደሚገባ አቶ አርአያ ተናግረዋል።
Source:Etv

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman