ትራምፕ በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰሱ ሶስተኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነዋል



ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ታህሳስ 09/2012(TW)

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ደምፅ ሰጠ።
ትናንት ምሽት ዘለግ ያለ ክርክር በጉዳዩ ላይ ያደረገው የሀገሪቱ ኮንግረስ ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም እና የኮንግረሱን ስራ ሆን ብለው በማሰናከል ወንጀሎች በምክር ቤቱ እንዲከሰሱ ድምፅ ሰጥቷል።
በዚህም ከፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገንና ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን በኋላ ሶስተኛው ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
በኮንግረሱ የሪፐብሊካን እና ዴሞክራቶች አባላት ረዥም ክርክር አድርገዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተከሰሱት ዩክሬን በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራቶችን ለመወከል እየተፎካከሩ ባሉት ጆ ባይደን ላይ ምርመራ እንድታደርግ ግፊት በማድረግ እና ይህን ክስ ለማጣራት የሚደረገውን ጥረት ባለመተባበር፣ ምስክሮች እንዳይመሰክሩ በመከላከል እና መረጃ በመከልከል የኮንግረሱን ተግባር በማደናቀፍ ወንጀል ነው።
ከክርክሩ በኋላ ወደ ደምፅ አሰጣጡ ሲኬድ የመጀመሪያው ክስ ላይ ከኮንግረሰ አባላት መካከል 230 ደግፈውት 197 ደግሞ ተቃውመውት አልፏል፤ ሁለተኛው ክስ ደግሞ
229 ድጋፍ እና በ198 ተቃውሞ ይሁንታን አግኝቷል።

ኮንግረሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ድምፅ ሲሰጥም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚችጋን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ውለዋል።.
ኮንግረሱ ውሳኔውን ማሳለፉን ተከትሎ ጉዳያቸው በሀገሪቱ ሴኔት መታየት ይጀምሯል።
ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱም ክሱ የሴኔቱን አባላት ሁለት ሶስተኛ ድጋፍ ማግኘት አለበት።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman