በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ላለው ግድብ አለመግባባት ጦርነት መፍትሄ አይሆንም -የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታ አል-ሲሲ


ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ታህሳስ 09/2012(TW)
አል-ሲሲ በግብጿ የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ሻርመ ኤል ሼህ ከተማ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ በግድቡ ዙሪያ በቀጣይ ወር የአሜሪካ ተወካዮች በሚገኙበት በዋሽንግተኑ ስብሰባ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ነው ትኩረት መሰጠት ያለበት ብለዋል።
"ያሉን ውስን ሃብቶች በጦርነት እና በግጭት መባከን የለባቸውም። ህዝቡን እና ሃገራችንን ለማልማት ልንጠቀምበት ይገባል"
ጦርነት መልስ አይሆንም የሚለው የአል-ሲሲ ንግግር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፓርላማ ላይ ለተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (/) ንግግር ምላሽ የሰጡ ይመስላል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥቅምት 11 2012 . በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ "የማንንም ፍላጎት ለመጉዳት የጀመርነው ፕሮጀክት አይደለም" ያሉ ሲሆን፤ "ቁጭ ብለን እናወራለን፤ ማንም ይህንን ግንባታ ማስቆም አይችልም። ይህ ሊሰመርበት ይገባል" ብለው ነበር።

በወቅቱ ከግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሰነዘሩ የጦርነት እንከፍታለን መልዕክቶችን አስመልክተው ሲናገሩ፤ "ማንንም አይጠቅምም [ጦርነት] ብለን እናምናለን . . . ጦርነትም ከሆነ ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ አላት፤ በሚሊዮን ማሰለፍ እንችላለን" ማለታቸው ይታወሳል።
በሻርም ኤል ሼክ ጋዜጠኞችን ያነጋገሩት አል-ሲሲ ዋናው ነገር በመጪው ወር በአሜሪካ ዋሽንግተን በሚደረገው ንግግር ዘላቂ መፍትሄ ላይ መድረስ ነው ብለዋል።
"ስለ ራሳችን ኃያልነት ብዙ ማለት አንፈልግም። ግን ሚሊዮኖችን ትመለምላለህ ወይስ ግድብ ትገነባለህ?" ሲሉ ጠይቀዋል።
"ሚሊዮኖችን በሚቀጥፍ ግጭትና ጦርነት ሃብታችን ሊፈስ አይገባውም። ይልቁንም ያን ገንዘብ ለህዝብና ለአገር ልማት እናውላለን" ሲሉ አል-ሲሲ ተደምጠዋል።
ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይቶች ውጤት አልባ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።
በዚህም የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች የተገኙባቸው የውይይት መድረኮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

VIA:BBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman