ፌዴራሊስቶች vs አሃዳዊስቶች



ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ታህሳስ 09/2012(TW)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮያን የፖለቲካ አየር ከተቆጣጠሩ ቃላቶች ዋናኞቹ ፌዴራልስቶችና አሃዳዊያኖች የሚሉት ናቸው።እንዲሀም ቀጣዩ ምርጫ በእነዚሁ ቡድኖች መካከል እንደሚሆን የሚተነብዩ አሉ ይህ አስገራሚ ነገር አይደለም በመሬት ላይ የሚታይ እውነታ ነው። ገራሚው ነገር / ዐቢይ የሚመራውን ብልፅግና ፓርቲን ከአሃዳዊያን ወገን መፈረጃቸው ነው።
እውን ብልፅግና ፓርቲ አሃዳዊነትን ለማስፈን ይታገላል ወይ? የሚለውን ነገር ከመመለስ ይልቅ ብልፅግና ፓርቲ አሃዳዊነትን ማምጣት ቢፈልግ እንኳ ማምጣት ይችላል ወይ?በሚለው ላይ መነጋገር ይቀላል።
በእኔ እምነት ብልፅግና ፓርቲ አሃዳዊነትን ማስፈን ቀርቶ ፌዴራሊዝምን ተቀብሎ እንኳን geographical federalizim ማድረግ የማይችልና የማያስብ መሆኑን በምክንያቶች አስረግጬ ለመናገር እወዳለሁ።
አንድን ስርዓት ለመመስረት ወሳኝ የሆኑ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ጥቂቶቹ የዓለምና የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ የዜጎቹ ማህበራዊ ስነልቦናዊ ባህላዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ወሳኞች ናቸው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ባካሄደው መራር ትግል የመሬት የብሄር ጉዳይ ላይ ድልን ቢቀዳጅም የዲሞክራሲና የእውነተኛ ፌዴራሊዝም ተጠቃሚ ባለመሆኑ ለዚሁ መብት በፅናት በመታገል አሁን በስልጣን ላይ ያለሁን የለውጥ ሀይል ወደፊት አምጥቷል ከዚህ የለውጥ ሀይል የሚጠብቀው ትክክለኛ ፌዴራሊዝም መሬት እንድይዝ ነው ይህ ሁኔታ ባለበት ፌዴራሊዝሙን ማፍረስ አሊያም ወደ ጂኦግራፊያዊ ለመመለስ መሞከር ራስን ከማጥፋት suicide የሚዘል እንደማይሆን ለማወቅ ፖለቲከኛ መሆን አያስፈልግም።አሁን አገር የሚመሩ ሰዎች ይህንን የማወቅ ዕውቀት ያጥራቸዋል ብዬ አልገምትም

ሁለተኛው ምክንያት አሁን ተዋህደው ብልፅግናን በመመስረት ሂደት ላይ የሚገኙ ፓርቲዎች ለሩብ /ዘመን ብሄርን መሠረት ላደረገ ፌዴራሊዝም የታገሉና በርካታ መስዋእትነት የከፈሉ ይህንን ስርዓት ወደተሟለ ደረጃ እንወስዳለን ብለው ሲሰሩ የኖሩ እንደመሆናቸው መጠን በቀላሉ ፌዴራሊዝሙን አፍርሰው አሃዳዊ ይሆናሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነትና ኢህአደግን አለማወቅ ነው።
ሶስተኛው ምክንያቴ ከአማራና ኦሮሞ በላይ ለዚህ ፌዴራሊዝም ጠንቃቃ የሆኑት እነ ሱማሌ አፋር ቤንሻንጉል ወዘተ ብልፅግና ፌዴራሊዝሙን ቢነካ ወይም ትንሽ እንኳን ቢጠራጠሩ ወደ ውህደቱ ባላመሩ
አራተኛዉ ምክንያቴ ብልፅግና ፓርቲ ባዘጋጀው ማኒፌስቶ ህገ ደንብ ፕሮግራምም ሆነ እከተላለሁ ባለው የመደመር ፍልስፍና አንዳች ቃል ወይም ሀረግ ፌዴራሊዝምን ስለመንካት አላነሳም
ከእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች በመነሳት ብልፅግና አይደለም አሃዳዊ መንግስት ሊመሠርት ጂኦግራፊያዊውን እንኳን ወደ ማድረግ እንደማይጓጓ ግልፅ ነው
VIA:Alaka Sinbiru

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa