አቶ ሌንጮ ለታ ለፊንፊኔ ነዋሪዎች ያቀረቡት ገራሚ ዛቻ መሰል ጥሪ



የቀድሞው ኦነግ ምክትል ዋና ፀሃፊ አቶ ሌንጮ ለታ ባለፈው ሳምንት በኢሳት ብቅ አሉና ለፊንፊኔ ነዋሪዎች እንዲህ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ


ቶ ሌንጮ ‘’ሁን ወያኔ ሊወድቅ ከጫፍ ላይ ደርሷል የስርዓቱ መሰረት የሆነው የኦሮሞ ሕዝብም ተነቃንቋል ለዚህ ንቅናቄ የፊንፊኔ ነዋሪዎች ድጋፍ ማድረግ አለባቸው አለበለዚያ  ኋላ መጠያየቅ አይቀርም” አሉ።

የኦሮሞ ሕዝብ የአሁኑ ፌዴራላዊ ስርዓት ምሰሶና ማገር መሆኑን በቅጡ የማያውቁት ወይም ማወቅ ያልፈለጉት አቶ ሌንጮ ለታ ከሰሞኑ ከሞቱበት ተነስተው አዋራቸውን በማራገፍ የተፍጨረጨሩ ትምክህተኛና ጠባብ ኃይሎች ሲንጫጩ ለአዲስ አበባ የተቃረቡ መስሏቸው በቱልቱላው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አማካይነት ካሉበት በስካይ ፒ ላይ ቀርበው ለከተማዋ ነዋሪዎች ይህን ከንቱ ጥሪ አሰሙ።

ወያኔ መገልበጡ እንደማይቀር በልበ ሙሉነት ተስፋ ያደረጉት ይህ ሰው በአስገራሚ ሁኔታ የፊንፊኔ ነዋሪዎች ትግሉን ተቀላቅላው ድምፃቸውን አንዲያሰሙ አሳሰቡ፤ይህ ካለሆነ ግን አሉ አቶ ሌንጮ ይህ ካልሆነ ግን ነገ መጠያየቅ አይቀርም አሉ፤ይህቺ ማሰፈራሪያ ዛቻ መሆኗ ነው።

ኦነግን ፈንግለው ሌላ ድርጅት መስርተው  እዚያው ውጭ አገር ተሸሽገው የሚገኙት አቶ ሌንጮ ምናልባት ቀድሞ ኦነግ ውስጥ በቆዩበት ወቅት ባፈሩት ዝና ተቀባይነት ሊኖራቸው ይችላል ብሎ ቃለ መጠይቅ ላደረገላቸው የአሸባሪው ቡድን ጋዜጠኛ  ብዙ ነገር ዝክዝክ አድረገው ተናግረዋል።የሽግግር መንግስቱ ሁኔታ፤የበደኖው እልቂት እንዲሁም የአርባ ጉጉው ጭፍጨፋም ትዝ ብሏቸው ብዙ ነገር አውርተዋል።

”ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ”ለአቶ ሌንጮና መሰሎቻቸው ጋብዣለሁ።ከሰውዬው ተስፈኛ ጥሪና ዛቻ ጋር በተያያዘ ብዙ ነገር መከተብ ብችልም ካረጁና ካፈጁ ጋር ክርክር መግጠም ጉንጭ ማልፋት ነውና ትቻለሁ።ደህና ሁኑ ጤና ይስጥልኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman