የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኘውን ልዩ ጥቅም የሚያጠና ግብረ ኃይል ተቋቋመ



ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከአዲስ አበባ ከተማ ሊያገኝ ስለሚገባው ልዩ ጥቅም የሚያጠና ግብረ ኃይል አቋቋመ፡፡ የተቋቋመው ግብረ ኃይል በክልሉ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች የተዋቀረ መሆኑ ታውቋል፡፡ 1987 .. የፀደቀው ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49(5) ላይ እንደተደነገገው፣ የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡

 
ኦሮሚያ ክልል ስለሚያገኘው ልዩ ጥቅም በዝርዝር በሕግ እንደሚወሰ ሕገ መንግሥቱ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ 20 ዓመታት ቢቆጠሩም ዝርዝር ሕጉ ባለመውጣቱ፣ በተለያዩ ምሁራን ጥያቄ ሲነሳ ቆይቷል፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ካቢኔ አባልና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ማግኘት ያለበት ልዩ ጥቅም እየተጠና ነው፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈሩ ድንጋጌዎች በሙሉ ተተርጉመው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል ማለት አይቻልም፡፡  

ምክንያቱም ሕገ መንግሥት ትልቅ ፍኖተ ካርታ (ሮድማፕ) ነው፤›› በማለት ሕገ መንግሥቱ በርካታ ጉዳዮችን አቅፎ መያዙን አቶ ፈቃዱ አስረድተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ትላልቅ ጉዳዮች ተለይተው መሠራታቸውን አቶ ፍቃዱ ገልጸው በተለይ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን የማስተዳደርና የመልማት ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሲሠራባቸው እንደቆዩ አመልክተዋል፡፡
 
ክልሉ እነዚህ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲሠራ የቆየ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ሁሉም ሥራዎች መልክ በመያዛቸው ወደ ልዩ ጥቅም ጉዳይ መገባቱን አስረድተዋል፡፡ ልዩ ጥቅም የማያካትትቸው ጉዳዮችና ከአዲስ አበባ ጋር በጋራ ለማደግ መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች በጥናቱ ምላሽ ይሰጣል ተብሏል፡፡

Source:Ethiopian reporter

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman