ሕገ መንግስታዊውን ስርዓት ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ ኃይሎች እንደሚቀጡ የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ



መንግስት በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎችና በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ሁከትና ጥፋት የመሩ የሽብር ሀይሎች ተላላኪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል


በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎችና በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ሁከትና ጥፋት የመሩ የሽብር ሀይሎች ተላላኪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት አስታወቅል።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና ተያያዥ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው የማብራሪያ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ የልማት እቅድን መሰረት አድርጎ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተነሳውን የግልፅነት ጥያቄ ተገቢ ብለውታል።

እቅዱን 2006 ይፋ ማደረጉን ተከትሎ መንግስት በበቂ ሁኔታ ግልፅነት መፍጠር አለመቻሉ በእጥረትነት እንደሚወሰድም ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ይህንን ክፍተት ተጠቀመው የህዝቡን ሰላማዊና ህጋዊ የግልፅነት ጥያቄ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የመሩት ፀረ ሰላም ሀይሎች ናቸው ብለዋል።

የፀረ ሰላም ሀይሎቹ መሰረት የሌለው የሀሰት መረጃ በማሰራጨት የራሳቸውን አጀንዳ ለማራገብና የህዝቡ ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄ ወደ ሁከትና ጥፋት የመሩት አካላት ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ አስረድተዋል።

አጋጣሚውን ተጠቅመው ድበቅ አጀንዳቸውን ለማስፈፀም የሰው ህይወትና ንብረት እንዲጠፋ እንዲሁም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የተንቀሳቀሱ ተላላኪ ሀይሎች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል።

ድብቅ አጀንዳቸውን ለማስፈፀም የተንቀሳቀሱት ፀረሰላም ሀይሎች በህጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ጭምር ሰርገው በመግባት የህዝቡን ጥያቄ ለመጠምዘዝ የተንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች ተላላኪዎች መኖራቸውን መንግስት በመረጃ ማረጋገጡን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። የማያዳግም እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል።

መንግስትም ወደ ህዝቡ ወርዶ ተከታታይ ውይይት እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል።

በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ዞን ከቅማንት ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ግጭት የፀረ ሰላም ሀይሎች እኩይ ድርጊት እንደሆነ አመልክተዋል። የክልሉ መንግስትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለቅማንት ማህበረሰብ የማንነት ዕውቅና የሰጠ ቢሆንም ችግሩ ሀገሪቱን ለማተራመስ የተነሱ ፀረ ሰላሞች አጀንዳ በመሆኑ ህዝቡ ራሱ ይታገለዋል ብለዋል። ችግሩን በማባባስ ውድመት እንዲከሰት ያደርጉ ወገኖችም በህግ እንደሚጠየቁ ተናግረዋል።

በአንዋር መስጊድ ላይ የተከሰተው ፍንዳታ ጉዳይ በምርምራ ላይ መሆኑን አስረድተው፣ መንግስት ምርመራውን ሲጨርስ ለህዝብ ያሳውቃል ብለዋል።።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መሸጥም ሆነ መለወጥ በህጋዊ መንገድ ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም፣ ከደቡብ ሱዳን ጦርነት ጋር ተያይዞ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ወደ ሀገር ለመግባታችው በምክንያትነት አስቀምጠዋል። የፀጥታ ሀይሎችም በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ ላይ ጥብቅ ቁጥጥሩ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግርን ለመፍታት መንግስት ህዝቡን ይዞ ዳር እንደሚያደርሰው ቃል ገብተዋል።

ውስብስብ የሆነውን የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሀገር ህልውና ጉዳይ በመሆናቸው መንግስት ህዝቡን እያሳተፈ የጀመረውን እርምጃ ያጠናክራል።

በሌላ በኩል መንግስት የኢትዮጵያን ቆርሶ ለሱዳን የሰጠው መሬት አለመኖሩን አስረግጠዋል። ይልቁንም ጉዳዩን የፀረ ሰላም ሀይሎች ሴራ ነው ብለዋል።

ሁለቱ ሀገሮች ቀድሞ የቆየውን የድንበር ማካለል ሂደት እውን ለማድረግ የጋራ የድንበር ኮሚሽን መስረተው በድርድር ለመፍታት እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። መንግስትም ለህዝቡ ሳያሳውቅ የሚሰጠው መሬት አይኖርም ብለዋል። የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠልሸት የሚወራውን ሀሰት ህዝቡ እንዲታገለውም አሳስበዋል።

በአየር መዛባት የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም እየተወሰዱ ስላሉ ስራዎችም ለምክር ቤቱ አባላት አብራርተዋል።

50 ዓመት ታሪክ ውስጥ አሁን የደርሰው ድርቅ ከባድ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ መንግስት እያድረገ ካለው ድጋፍ ባሻገር እስካሁን አርሶ አደሩ ባለው ጥሪት ጭምር ህይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስ ችግሩን ለመቋቋም መቻሉ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

በውሃ ቦቴ ውሃ ከማሰራጨት ባሻገር ድርቁ በጠናባችው አካባቢዎች ችግሩ መዋቅራዊ እየሆነ በመምጣቱ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋም እየተሰራ እንደሆነም አመልክተዋል። መንግስት አልሚ ምግብን ጭምሮ የእህልና ዘይት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman