ልክ እናስገባቸዋለን? የማሸማቀቂያ ስልት


የአገራችን ሕገ መንግስት አብዛኛው የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ተስማምተውበት ተግባራዊ በመሆን ላይ የሚገኝ ወርቅ ሕገ መንግስት ነው።

የቀድሞ ስርዓቶችን በመናፈቅና ርካሽ ቡድናዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲሉ በኢህአዴግ እየተመራ ባለው ልማታዊ ዴሞክራሲያ መንግስት ላይ ጭፍን ጥላቻ የፈጠሩ ጥቂት  ጽንፈኛ ቡድኖች አሁንም የጥላቻ ፖለቲካቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ የጥላቻ እንቅስቃሴያቸውም እነርሱ እንደፈለጉ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ የፈጠረውን ሕገ መንግስት ጭምር በመናድ የኢትዮጵያን የእድገት ግስጋሴ ለመግታት የሚችሉትን ነገር ሁሉ በማድረግ በመረባረብ ላይ ናቸው።

በ2007 ዓ.ም. አገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ በህጋዊ መንገድ የተንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአብዛኛውን መራጭ ድምፅ ማግኘት ስላልቻሉ ኢህአዴግ እጅግ በጣም ከፍተኛውን ድምፅ ባገኘው መሰረት ከህዝቦች የተሰጠውን ከባድ አደራ ተቀብሎ አገር እያስተዳደረ ነው።

ተወደደም ተጠላ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የሰጡትን ከባድ አገር የማስተዳደር አደራ ተቀብሎ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል።የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታም በኢህአዴግ መስመርና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ውሳኔ እንጂ በጥቂት ቆርጦ ቀጥል ቡድኖች የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሚወሰን አይደለም።

የውስጥ ኪራይ ሰብሳቢዎች ፍላጎት

በአገር ውስጥ የሚገኙ ኪራይ ሰብሳቢዎች የኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት እንዳይቀጥል ባላቸው ፅኑ ፍላጎት መክንያት ሰላም እንዲናጋ ይፈልጋሉ፤በውጭ የሚገኙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳም በአገር ውስጥ ተቀባይነት አግኝቶ አሁን ያለው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲናጋ ይመኛሉ ለዚህም የሚችሉትን ድጋፍ በማድረግ ላይ እንዳሉ ይታወቃል።

ለምሳሌ በማስተር ፕላን ምክንያት በአንዳንድ የኦሮሚያ ትምህርት ቤቶች ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግርግር በቍጥጥር ስር ውሎ እያለ በመላ ኦሮሚያ ተባበሶ የቀጠለ መሆኑን በማስመሰል የሃሰት መረጃዎችን ይሰጣሉ፤በአገር ውስጥም ዜጋው እንዲሰጋ በመፍጨርጨር ላይ ናቸው።

ለዚህ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በመስራት ላይ የሚገኙ የውስጥ ኪራይ ሰብሳቢዎች እንዳሉ ግልፅ ነው።ለዚህ ደግሞ መነሻ የሆነው በኢህአዴግ እየተመራ ያለው መንግስት ኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ቍርጠኛ አቋም ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ ነው።እነዚህ የውስጥ ኪራይ ሰብሳቢዎች በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ የተጀመረው እርምጃ ቀጣይነት እንዳይኖረውና መንግስት ሌላ አጀንዳ ላይ አትኩሮ እነርሱም የቀራረሟትን ለማሸሽ ጊዜ እንዲያገኙ ይፈልጋሉ።ስለዚህም የማስተር ፕላኑ ጉዳይ አሳሳቢ ነው፤ተቃውሞ በዝቷል፤በድርቁ ምክንያት የዜጎች ሕይወት እየጠፋ ነው ሲሉ ይደሰኩራሉ።

የአቶ በቀለ ነጋ መሰረተ ቢስ ክርክር


አባዱላ ገመዳ ምን አሉ?
በ2006 ዓም በማስተር ፕላን ሰበብ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ተቃውሞ ትክክል አለመሆኑን እና ተማሪዎቹ ሳይገባቸው በፅንፈኛ ጠባብና ትምክህተኛ ኃይሎች አጀንዳ መጠለፋቸውን ከተማሪዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነግረዋቸዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቶ አባ ዱላ የተማሪዎች ጥያቄ ትክክል ነው ብለው ተናግረዋል በሚል የሚነዛው አሉባልታ መሰረት ቢስ ነው።በወቅቱ ተማሪዎቹ ትክክል ናቸው ብለው የተናገሩት በደሞክራሲያዊ መብት ተጠቅማችሁ በማንም ላይ ጉዳት ሳይደርስ ጥያቄአችሁን ለማቅረብ ያደረጋችሁት ጥረት ትክክል ነው ማለታቸው የታወቀ ቢሆንም ይህን አባባል ለራስ ፕሮፓጋንዳ በሚመች መልኩ መጠቀም ከውድቀት የሚያድን አይሆንም።

በወቅቱ በአምቦ በተከሰተው  ተቃውሞ የመንግስትና የግለሰቦች ንብረት ወድሟል፤ታዲያ አቶ አባዱላ ገመዳ እንዴት ሆኖ ነው ይህ ድርጊት ትክክል ነው ብለው የሚናገሩት?

እሳቸው ባላቸው ኃላፊነትና ተሰሚነት ተጠቅመው የዋህ ተማሪዎች በፅንፈኞች አነሳሽነት ጉዳት ላይ እንዳይወድቁ ማድረጋቸው እጅግ የሚያስመሰግናቸው ነው።

ልክ እናስገባቸዋለን?

አቶ አባይ ፀሃዬ ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ካልሆነ ልክ እናስገባቸዋለን ብለዋል በሚል በOMN አራጋቢነት የሚነዛው  ወሬም ምንም መሰረት የሌለው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።አቶ አባይ በዚህ ጉዳይ ላይ በምንም አይነት ሁኔታ እንዲህ እንደማይሉ የሚታወቅ ቢሆንም ፅንፈኞች ግን በቆርጦ ቀጥል ስልታቸው በዚህ አባባል ተጠቅመውበታል።አቶ አባይ ሻዕቢያዎችን ልክ እናስገባቸዋለን ማለት ይችላሉ፤የኦሮሞን ሕዝብ ግን ልክ እናስገባለን ብለው እንደማይናገሩ ማንም ሊረዳ ይችላል።

ይህ የቆርጦ ቀጥሎች ስልት የተቀነባበረው ጠንካራው የሕወሃት አባልና የታላቁ ኦሮሞ ብሄር ዴሞክራሲያዊ ትግል እንዲጠናከር በቍርጠኝነት ከሚያደርጉት ትግል ወደ ኋላ ለመመለስና ለማሸማቀቅ የተደረገ እኩይ ተግባር ነው።

አቶ አባይ የኦሮሞ ሕዝብ ትክክለኛ አታጋይ ድርጅት ኦህዴድ እንዲመሰረትና ሁሉም የኦሮሞ ተወላጆች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሰሩና በመስራት ላይ የሚገኙ ድንቅ የኦሮሞ ወዳጅና ተቆርቋሪ ታጋይ ስለመሆናቸው ለኦሮሞ ብሄር አይነገርም።ጤና ይስጥልኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa