ኦሮሚያን በመገንጠል የሕዳሴ ጉዞን ለማደናቀፍ?



ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለው ሁኔታ ለሁሉም አሳሳቢ ነው።ችግሩ የኦሮሚያ ክልል ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ወገኖች ካሉ እነርሱ በእርግጥ ተሳስተዋል።


ከሕገ መንግስቱ አንፃር ሲታይ በቅድሚያ የክልሉን ሰላምና መረጋጋት አስተማማኝ ማድረግ የሚችለው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ነው።በዚህም መሰረት የክልሉ የሰላም ኃይሎች ሰሞኑን ጠባብና ትምክህተኛ ኃይሎች  አብረው በማስተር ፕላን ሽፋን የቀሰቀሱትን ሁከት ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።ሌሎች የአገራችን የሰላም ኃይሎችስ ምን እያደረጉ ነው?እዚህ ላይ የሰላም ኃይል ሲባል የታጠቀውን ክፍል ብቻ እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል።

የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ለዘመናት ተካባበረውና ተዋደው ሰላምን በማረጋገጥ አብረው ኖረዋል።ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ከየትኛውም የአገራችን  ብሄር ብሄረሰብ ጋር  በአንድነት እየኖረ ያለው ኩሩው የኦሮሞ ብሄር ነው።ይህ አኩሪና ተደናቂ የሆነ አብሮነት አሁንም ቀጥሏል።የአብሮነቱ ጉዞ እንዳይቀጥልና በተለያዩ ምከንያቶች ተደናቅፎ ከመንገድ እንዲቀር ግን በጠባብነት በትክህተኝነትና በአክራሪነት የተጀቦኑ ኪራይ ሰብሳቢ ኃይሎች የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ በመፍጨርጨር ላይ ናቸው።

ኪራይ ሰብሳቢው ኃይል የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ሃቀኛ ለመምሰልና ራሱን ለመከላከል ቢፍጨረጨርም ከቁርጠኛ የመንግስት አካላትና ከሕዝቦች የበለጠ አቅም የለውምና የትም መድረስ አይችልም።እዚህ ላይ ከሕዝብ የተደበቀ ምንም ነገር የለምና ለዘላቂ ሰላማዊ ሁኔታ መረጋገጥ ህገ ወጦችን በማጋለጥ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል።የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ ጥረት ሰላማቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ።

ሚዲያዎቻችን

የአገራችን ሚዲያዎች የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ ከመስራት ጎን ለጎን አሁን በኦሮሚያ የተፈጠረው ሁኔታ ተወግዶ አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ ማድረግ ይችላሉ።በአገራችን የሚገኙ የግሉም ሆነ የመንግስት መገናኛ ብዙሃኖች ባለፉት አመታት በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በየትኛውም የአገራቸው ጉዳይ ላይ ሰርተው ሕዝቦችን ማነቃነቅ የሚያስችል አቅም ገንብተዋል።

በዚህ አቅም ተጠቅመው የአገሪቱንም ሕጎች በማክበር በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ትክክለኛ ዘገባዎችን ለአንባቢና አድማጭ ተመልካቾች በማቅረብና በማጋለጥ  የፀረ ሰላም ኃይሎችን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ ትግሉን ማፋፋም ይጠበቅባቸዋል።እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ የለሁበትም አያገባኝም በሚል ዝምታን መምረጥ ኋላ ላይ ከባድ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል።ሚዲያዎችም ሰርተው ራሳቸውን በመጥቀም ቀጣይ መሆን የሚችሉት የአገራችን ሰላምና ዴሞክራሲ ቀጣይነት ሲረጋገጥ ብቻ በመሆኑ ነግ በኔ ብለው መስራት ተገቢ ነው።

በአሁኑ ወቅት እጅግ አንገብጋቢ የድርቅ አደጋ፤የኪራይ ሰብሳቢነትና የመረጋጋት አገራዊ ጉዳዮች እያሉ ሙዚቃን ማስደለቅና በአርሴና ማንቼ ጉዳይ ላይ ብቻ ማትኮር የትም አያደርስም።

በተለይ የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዝምታው ለክልሉም ሆነ ለአገሪቱ አይጠቅምምና ከዝምታና እንቅልፍ ከተጫጫነው ጉዞ ወጥቶ  ትክክለኛ መረጃዎችን ለሕዝብ ማቅረብ ይጠበቅበታል።የግንቦት 7 ኢሳት፤የአዲሱ ኦነግ ሚዲያ OMN እና የሌሎች ሚዲያዎችን አፍራሽ አካሄድና ዘመቻ ማክሸፍ የሚቻለው ይህ ሲሆን ብቻ ነው።


የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ለዘመናት ባካሄዱት መራራ ትግል በእጃቸው ያስገቧቸውን ድሎች ማጣት በፍፁም አይፈልጉም።ባለፉት አመታት በፖለቲካ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ያስመዘገቧቸውን እጅግ ጣፋጭ  የትግል ውጤቶችን በመንከባከብ ግስጋሴያቸው ወደ ፊት እንጂ ለአፍታም ቢሆን ወደ ኋላ እንዲመለስ የማይፈልጉ መሆናቸውን በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ባሳላፏቸው  ውሳኔዎች አረጋግጠዋል።

የሕዝቦች ትግል ጉዞ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ እንደማይጓዝ የታወቀና የተረጋገጠ ጉዳይ ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በቁርጥ ቀን ልጆቻቸው እልህ አስጨራሽ ትግል የተጎናፀፏቸውን ድሎች ለመንጠቅ የተለያዩ ኃይሎች በመፍጨርጨር ላይ መሆናቸው ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል።

የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች?

በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየትኛውም ምክንያት አሁን ያለው ስርዓት ከስልጣን እንዲወገድላቸው ይሻሉ፤ይህ ፍላጎታቸው እንዲሳካ ደግሞ የሰላም መደፍረስ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል ከዚህ በኃላ ድርድር፤አገራዊ እርቅ ብሄራዊ መግባባት  ምንትሴ ቅብጥርሴ ለማለት ይመቻቸዋል።አሁን አንዳንዶቹ በኦሮሚያ የተፈጠረውን ሁከት ለማጋጋል ብርቱ ጥረት በማደረግ ላይ ናቸው፤ ሌሎቹም አድፍጠው በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል።


የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ምን እየሰራ ነው?

ይህ ፓርቲ የኦነግና የግንቦት 7 አሸባሪ ድርጅቶች ተልዕኮ አስፈፃሚ ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።ይህን በማደረግ ላይ የሚገኘው ህጋዊና ህገ ወጥ አካሄድን በመጠቀም ነው።በተለይ ሰሞኑን በኦሮሚያ የተከሰተው ሁከት እንዲባባስና ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ሕፃናት ተማሪዎች ተነሳስተው ለጉዳት እንዲዳረጉ በመቀቅሰቀስ ላይ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ተረጋግጧል።

ለዚህም ከውጭ በተሰጣቸው ተልዕኮ መሰረት ተማሪዎች በማያውቁት ጉዳይ እንዲሳተፉ የኦሮሞ መሬት እየተዘረፈ ነው አትነሳም ወይ ምን ትጠብቃለህ እያሉ ሲቀሰቅሱና አብረው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የድርጅቱ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው በቂ ማስረጃ ነው።

በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አቶ በቀለ ነጋ በሁከቱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አጋንነው በማቅረብና እስክርቢቶ ያየዙ ተማሪዎች እየተጨፈጨፉ ነው ሰሉ ለተለያዩ የውጭ አገር ሚዲያዎች የሚሰጡት መግለጫ በእስር ላይ ያቆያቸውን መንግስት እየተበቀሉ መሆናቸውን አስመስክሮባቸዋል።

ሰሞኑን ለብሉንበርግ፤ለቪኦኤና ሌሎች የውጭ ሚዲያዎች በየዕለቱ የሚሰጡት መግለጫ ሰውዬው ለብቀላ ታጥቀው መነሳታቸውን ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa