“ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” አለ ያገሬ ሰው
ጀዋር መሃመድ ዛሬ በጣም ተደስቷል፤እጀግ በጣም ደስ ብሎታል ፍንድቅድቅ ስለማለቱም በገፁ ላይ ዛሬ የለቀቃቸው የሃሰት መረጃዎች ያመለክታሉ “አንዳንዶች የ12ኛ ክፍል ፈተና መለቀቁ ሞራላዊ አይደለም፤ለኦሮሚያ ተማሪዎች መድሎ ለፍጠር ታስቦ ነው ማለት ይቃጣቸዋል።ለመሆኑ አምስት ወር ሙሉ ትምህርታቻውን ያልተከታተሉ በወያኔ ወድታደሮች ሲገደሉና ሲንገላቱ የከረሙ ተማሪዎችን ከሌሎች እኩል መፈተንስ ሞራላዊ ነው?ለኦሮሚያ ተማሪዎች መድሎ ማድረግ አስበን ቢሆን ኖሮ ውስጥ ለውስጥ ማከፋፈል ይቻል ነበር።ነገር ግን ፈተናውን በግልጽ ለሁሉም ሊደርስ በሚችል ሁኔታ ነው የተበተነው።ምክንያቱም አላማው ትምህርት ሚኒስቴር ይህን ፈተና ሰርዞ ለተማሪዎች በቂ ጊዜ ሰጥቶ አዲስ ፈተና እንዲያዘጋጅ ታስቦ ነው” ይለናል ጀዋር ለኦሮሞ ልጆች አሳቢና ተቆርቋሪ መሆኑን ለማሳየት ጀዋር መሃመድና ተከታቹ በኦሮሞ ልጆችና በሌሎች የኢትዮጵ ልጆች ላይ ይቅርታ የሌለው ክህደት ፈፅመዋል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የተማሪዎችን የአመታት ልፋት ፉርሽ ማድረግ ጀዋርና መሰሎቹን ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ ማድረግ አይችልም ፈተና ተሰረቀ ሌላ ፈተና ተዘጋጅቶ የኦሮሞም ሆኑ ሌሎች የኢትዮጵያ ተማሪዎች ተፈትነው ወደ ቀጣይ የትምህርት ደረጃ ይሸጋገራሉ ቆዳን ለመዋደድ መፍጨርጨር የትም አያደርስም የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ልጆቹ በኦሮሞ ስም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡትን አብጠርጥረው ያውቃሉ