በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት የለም እንዴ?
“በራስ ወዳድነትና በመሰሪ ራስ
ወዳድነት መካከል ልዩነት አለ እኔ ራሴን እወዳለሁ ራሴን ስለምወድ የግል ሃሳቤን በርዕዮተ አለም፤ለስጋ ዝምድና፤ለፓርቲ ፍቅር ስል
አልሰዋም እንዲሁም ለራሴ ያለኝን ፍቅር የሕዝብ ፍቅር፤የድርጅት ፍቅር በሚል መሰሪ ካባ አላለብሰውም” ይለናል በእውቀቱ ስዩም የተባለ
ፀሃፊ “ከአሜን ባሻገር” በተባለ መፅሃፉ መግቢያ ላይ
በኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ
ሙሉ መብት በሕገ መንግስታችን ላይ ዕወቅና አግኝቶ መብቱ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ በመሆን ላይ እያለ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት የለም
አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ ይሉናል የበእውቀቱ ስዩም አይነት ደፋሮች የሚሹትነትን ሁሉ እያሉ ባሉበት ዘመን
በውጭ አገራትም ሆነ በአገር ውስጥ
የሚገኙ አንዳንድ ኃይሎች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ የለም፤ይህ መብት ባለመኖሩ ምክንያት ብዙዎች ታስረዋል ተሰደዋል
ተጎድተዋል ሲሉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን ይነፉብናል ይደነፉብናል
ተጎድተው ተሰደዋል የተባሉቱ ወገኖች
ምን አድርገው ነው? የትኛውን ገደብ አለፉ? የአገሪቱን ሕግስ በምን አይነት ሁኔታ ነው የጣሱት? ብለው ለመጠየቅ እንኳ አይሞክሩም
በነገራችን ላይ የፕሬስ ነፃነት
ሲባል ጋዜጣና መፅሄቶች ላይ የሚሰራጨውን ሃሳብ ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል
በአገራችን በየወቅቱ ቁጥራቸው በመጨመር
ላይ የሚገኙት ሬዲዮ ጣቢያዎ፤የቴሌቪዢን ጣቢያዎች፤ታትመው ለአንባቢያን በመቅረብ ላይ የሚገኙት ኢህአዴግን የሚሸነቁጡ መፅሃፍቶች፤በማህበራዊ
ሚዲዎች በየደቂቃው በመሰራጨት ላይ የሚገኙ ሃሳቦችና ትችቶች በአገራችን ኢትዮጵያ የተሟላ የሃሳብ ነፃነት መብት ስለመኖሩ ማረጋገጫዎች
ናቸው
በተለይ በአሁኑ ወቅት በየጊዜው
ታትመው ለገበያ በመቅረብ ላይ የሚገኙ መጽሓፍቶች በአገራችን የሃሳብ በዝሃነት መኖሩን በሰፊው ያሳያል
ታዲያ እነ እንቶኔዎች ሃሳብን በነፃነት
የመግለፅ መብት ተደፍጥጧል እያሉ ኢትዮጵያን የሚከሱት ከጭፍን ጥላቻ በመነሳት አይደለም ትላላችሁ?ደግሞኮ ከኤርትራ ጋር ያነፃፅሩናል
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ