ውሸት ያኮሰሰው ዶላር ሲቃርም

ጀሌዎቹ ሲያንቆለጳጵሱት ፕሮፍ እያሉ ይጠሩታል የእነ ሲሳይ አጌና አይነቶቹ፤ በአሁኑ ወቅት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አሸባሪ ድርጅት ሊቀመነበር እንደሆነ የሚነገርለት ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በደቡብ በኩል ታጣቂዎችን በማስረግ ያስገባነው እኛ ነን ኃላፊነቱንም እንወስዳለን ሲል የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን ሲነፋ ተሰምቷል ይህም ኢህአዴግን በጭፍን  ከሚጠሉ የዲያስፖራ አባላት ጥቂት ዶላሮችን ለመቃረም ሊያግዘው እንደሚችል ይገመታል 


እንኳን ኃላፊነት መውሰድ የሆነው ነገር ምን እንደሆነ የማወቅ መንገዱም ሆነ ብቃቱ የሌለው ይህ ሰው አፉን ሞልቶ በድፍረት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አለን ሲል ቱሪናፋውን ነፍቷል

በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ ታጣቂዎቻችሁ በየት አካባቢ ነው ያሉት ብሎ ላቀረበው ጥያቄ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አለን የሚል ድፍረት ተሞለበት ምላሽ አግኝቷል

የኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር የጋራ ግብረ ሃይል የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎች ስማቸውን በመቀየር የኤርትራ የጉዞ ሰነድ ከተዘጋጀላቸው በኋላ ከአስመራ ተነስተው ወደ ኡጋንዳ በአውሮፕላን ቀጥሎም በተሽከርካሪ ወደ ኬኒያ ተጉዘው በሞያሌ በኩል ድንበር ተሻግረው በደቡብ ክልል በሚገኝ ጫካ ውስጥ ያልታወቁ መስሏቸው ራሳቸውን በመደበቅ መቆየታቸውን መግለፁ ይታወሳል።

ግብረ ኃይሉ እንዳስታወቀው በዚያም ለተለያዩ የሽብር ተግባራት ሲዘጋጁ  በተካሄደው  ኦፕሬሽን ሚያዚያ 28 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ውለዋል። በወቅቱ ለማምለጥ የሞከሩ ጥቂት አሸባሪዎችም ተገድለዋል።

ይህን እውነት ሽምጥጥ አድርጎ የካደው ብርሃኑ ነጋ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ኃላፊነቱን ወስደናል፤በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከኢትዮጵ ህዝብ ጋር እየታገልን ነው ሲል ራሱን ትዝብት ውስጥ ጥሏል

ዶክተር ብርሃኑ ምንም ይበል፤ውሸቱን በመደርደርም ዶላሩን ይቃርም ጅላጅል ዳያስፖራዎችም እንደለመዱት ይጃጃሉ ኢትዮጵያ ግን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን እየተከላከለች የህዳሴ ጉዞዋን ቀጥላለች፤የሻዕቢያ ተላላኪዎች በየትም አቅጣጫ ተሽሎክሉከው ይምጡ እንደተለመደው ዋጋቸውን ያገኛሉ



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman