ሂላሪ ክሊንተን ዴሞክራቶችን ለመወከል ከጫፍ መድረሳቸው እየተነገረ ነው

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የእጩዎች መረጣ ሂላሪ ክሊንተን ዴሞክራቶችን ለመወከል ከጫፍ መድረሳቸው እየተነገረ ነው። 


ከቬርሞንቱ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ ጋር እየተፎካከሩ ያሉት ሂላሪ ክሊንተን ትናንት ምሽት በተካሄደ ምርጫም በኬንታኪ በጠባብ ድምጽ ማሸነፍ ችለዋል።

በኦሪገን ግዛት በተደረገ ሌላ ፉክክር ደግሞ በርኒ ሳንደርስ ማሸነፍ ችለዋል።

ዴሞክራቶች አዛውንቱ ሳንደርስ መድረኩን ለሂላሪ ክሊንተን እንዲለቁ እየጠየቁ ነው፤ ሙሉ ትኩረታቸውን በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እንዲያውሉት በሚል።

ጠባብ የማሸነፍ እድላቸውን እንደሚሞክሩ የተናገሩት ሳንደርስ ግን እስከ ካሊፎርኒያው ምርጫ እንደሚወዳደሩ ገልጸዋል።

ዴሞክራቶችን ለመወከል በእስካሁኑ ፉክክር፥ ሂላሪ ክሊንተን 2 ሺህ 291 ድምጽ ሲያገኙ በርኒ ሳንደርስ በ1 ሺህ 528 የድጋፍ ድምጽ ይከተላሉ።

በሪፐብሊካኑ በኩል በእጩነት ለመቅረብ ድምጽ እያሰባሰቡ የሚገኙት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ምሽት በተካሄደው የኦሪገን ድምጽ አሰጣጥ ላይ አሸንፈዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman