የ14 ፖለቲካ ፓርቲዎች ፈቃድ ተሰረዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕጉና በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች እንዳላሟሉ የተረጋገጡ 14 የፖለቲካ ፓርቲዎች ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ።

ቦርዱ በህገ መንግስቱ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም እና በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ፣ እንቅስቃሴያቸውን የመከታተል፣ የመቆጣጠር፣ ድጋፍ የማድረግና ህጉን አሟልተው ባልተገኙ ጊዜ የመሠረዝ ሥልጣንና ኃላፊነት እንዳለው ተደንግጓል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ በመከታተልና በመቆጣጠር ሂደት ፓርቲዎች በህጉ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች አሟልተው እንዲንቀሳቀሱ በተለያዩ ጊዜያት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራር ጋር የጋራ ምክክር ማድረጉን ቦርዱ አስታውሷል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲዎቹ በህጉ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ጉዳዮች ማሟላት እንዳለባቸው ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠነ ሰፊ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መስራቱንም ነው የገለፀው፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ህጉን ሳያሟሉ በተገኙና ማስተካከያ እንዲያደርጉ እገዛ ተደርጎላቸው ባላሟሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ይታወቃል፡፡

በዚህ መሠረት ቦርዱ በሕጉና በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን የሕግ ጉዳዮች ላላሟሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላሟሏቸውን ድንጋጌዎችና አፈፃፀሞች በመዘርዘር በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም እና በፓርቲዎቹ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ የሚከተሉት 14 የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከአሁን ድረስ በሕጉና በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት ማሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች እንዳላሟሉ ተረጋግጧል፡፡

ለአብነትም ፓርቲዎቹ በመተዳደሪያ ደንባቸዉ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂዱበት ጊዜ ያለፈ በመሆኑና በአዋጁ አንቀፅ 21 ንዑስ አንቀፅ 1 በተደነገገው መሠረት የሥራ ጊዜያቸው በተጠናቀቀው አመራሮች ምትክ አዲስ የአመራር አባላትን መርጦ ወዲያውኑ ለቦርዱ ባለማሳወቅ ፣
በምዝገባ አዋጁ አንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ 1 /ሐ/ መሠረት በኦዲተር የተረጋገጠና በግንባሩ መሪ የተፈረመ የሃብትና እዳ ሰነድ የጽሑፍ ሪፖርት ባለማቅረብ፣

በምዝገባ አዋጁ አንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ 5 መሠረት ፓርቲው ያለውን ዋና ጽሕፈት ቤት እና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አድራሻ፣ የጽሕፈት ቤቶቹን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች ለቦርዱ በጽሑጽ ባለማሳወቅ፣

በአዋጁ አንቀፅ 23 ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3 መሠረት በሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተረጋገጠ የሞያ ብቃት ያለው በፓርቲው የተሾመ የውጭ ኦዲተርና የተሾመው ኦዲተር ሹመቱን መቀበሉን በፊርማው ያረጋገጠበት ሰነድ አለማቅረብ፣ ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡
በዚህም መሰረት፡-

1.የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት /ኢዴኃኅ/
2. የኮንሶ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ኅብረት /ኮሕዲኅ/
3. የኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ፓርቲ/ኢአምፓ/
4. ባሕረወርቅ መስመስ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ባመሕዴድ/
5. የጠንባሮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት /ጠሕዴኅ/
6. የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ሶጎሕዴድ/
7. የጋሞ ጎፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት /ጋጎሕዴአ/
8. የሐረሪ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሐሕዴፓ/
9. የጉራጌ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ጉሕዴግ/
10. የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት /ሶዴኃቅ/
11. የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት /ደኢዴኃአ/
12. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት /ጋዴኅ/
13. የሀዲያ ብሔራዊ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት /ሀብአዴድ/ እና
14. የአፋር ብሔራዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /አብአዴግ/

ቦርዱ ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ.ም ባካሄደው 006/08 መደበኛ ስብሰባው ጉዳዩን አስመልክቶ በጽሕፈት ቤቱ የቀረበለትን ማስታወሻ በስፋትና በጥልቀት ከመረመረ በኋላ ከላይ የተጠቀሱት 14 የፖለቲካ ፓርቲዎች በቦርዱ ውሣኔ ፈቃዳቸው እንዲሠረዝ ወስኗል፡፡


በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት 14 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በቦርዱ ውሣኔ ፈቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን ቦርዱ እየገለፀ፥ ፈቃዳቸው የተሰረዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲ መሰረዝ ወይም መፍረስ ውጤትን አስመልክቶ የተደነገገውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቦርዱ አሳዉቋል፡፡

Source:FBC

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman