አብዮት ልጇን ትበላለች?
ስለ አብዮት ሲነሳ በርከታ ጉዳዮችን
በማንሳት ከየአቅጣጫው ማየት ይቻላል እስኪ ስለ አብዮትና አብዮተኞች እንጨዋወት የአገሬን የፕሬስ ነፃነት በመጠቀም የማንንም መብት
ሳልጋፋ የምፈልገውን ለማለት ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ መብት አለኝና
ለውጥ እንፈልጋለን የሚሉ ሃይሎች
በተለያዩ ወቅቶች የሚያገኙትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ ይታያል ይህ ክስተት በአገራችንም ሆነ በሌሎች የአለም አገራት
የተለመደ መሆኑ ይታወቃል
የአሁኖቹ የአገራችን አብዮት አድራጊዎች
እንኳ “ሲሉ ሰምታ ዶሮ ታንቃ ሞተች”አይነት መሆናቸውን ከተጨባጭ ተግባራቸው ተረድተናል
በተለያዩ የአረብ አገራት “አረብ
ስፕሪንግ” በሚል ስያሜ ተቀስቅሶ አሳዛኝ ውደመቶችን ያስከተለው እንቅስቃሴ
የአገራቱን ኢኮኖሚ አውድሞ አልፏል የአገራቱ በርካታ ዜጎች ህይወትም ጠፍቷል አካለ ስንኩል ሆነው የቀሩም አሉ
የግብፅ አብዮተኞች የአገሪቱ አመራሮች
በተለያዩ ምክንያቶች የፈፀሟቸውን ስህተቶች ምክንያት አድርገው በመቃወም በጥቂት አመታት ልዩነት ውስጥ ሆስኒ ሙባረክንና ሞሃመድ
ሙርሲን በግድ ከስልጣን መንበር አሽቀንጥረዋል
ይህንና በሌሎች የአረብ አገራት
የተካሄደውን ግርግር የተመለከቱ አንዳንድ የአገራችን ተስፈኞችም በአረብ አገራት የሆነውን በኢትዮጵያም በመድገም ኢህአዴግን ከስልጣን
መንበር አሽቀንጥረው ለመጣል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም
የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳ ብናስታውስ
በኦሮሚያና አማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የነበረውን ሁከት የመሩት አብዮተኞች ፍላጎትና ድርጊት አብዮት ልጇን ትበላለች
በሚል የሚታወቀውን ብሂል አስታውሶን አልፏል ከኋላ ሆነው በለው ግፋው ብለው ሲገፋፉ የነበሩ እነ ጀዋር መሃመድና ሌሎች “የጠላቴ
ጠላት ወዳጄ ነው” ያሉ ጠባብና ትምክህተኛ ኃይሎች በሞቀ ቤታቸው ተቀምጠዋል በእነዚህ ክፉ ኃይሎች ባዶ ተስፋ የተነሳሱ ደሃ ወገኖቼ
ግን እንደወጡ ቀሩ አብዮት ልጇን ትበላለች?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ