አይሞቀው አይቀዘቅዘው ባለስልጣን ይዞ የህዳሴ ጉዞ?

ለእኔ እንደሚመስለኝ አይሞቀው አይቀዘቅዘው ባለስልጣን ይዞ መቼም ቢሆን የትም መድረስ አይቻልም

የአገራችን ስርዓት አደጋዎች በአግባቡ ተለይተው ታውቀዋል እነዚህ አደጋዎች ኪራይ ሰብሳቢነት፤አክራሪነትና ሽብርተኝነት እንዲሁም ጥበትና ትምክህተኝነት ተብለው ተለይተዋል ከእነዚህ ውጭ ያሉቱ እዳቸው ገበስ ነው ሁሉንም በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ በቀላሉ መፍትሄ ማግኘት የሚችሉ ናቸው ለማለት ነው

አፅንኦት ተሰጥቷቸው የተለዩ አነዚህ የስርአታችን አደጋዎች ግን ተወግደው ከአሳሳቢነት ደረጃ መውጣት የሚችሉት የሁሉም ወገኖች ያላሰለሰ ጥረት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል አለበለዚያ በተወሰኑ አካላት ጩኸትና ነጋ ጠባ ማላዘን ችግሮቹ ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት አይችሉም
በተለያዩ የኢህአዴግ ሰነዶች ላይ እንደ ተብራራውና በመድረኮች ላይም አፅንኦት ተሰጥቶት እንደሚነገረው የተጠቀሱት የስርአታችን አደጋዎች ማለትም ኪራይ ሰብሳቢነት፤አክራሪነትና ሽብርተኝነት እንዲሁም ጥበትና ትምክህተኝነት በአመለካከትም ሆነ በድርጊት ደረጃቸው ይለያይ እንጂ በሁሉም ውስጥ አሉ

ይህ ማለት ችግሮቹ በህብረተሰብ፤በድርጅትና በመንግስት ውስጥ ይገኛሉ ማለት ነው መቼም እኔ ፍፁም ነኝ ከእነዚህ አሳሳቢ ችግሮችም ነፃ ነኝ ብሎ የሚከራከር የሚኖር አይመስለኝም
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ስለመኖሩ ጉቦ መስጠትና መቀበል፤በአቋራጭ ተጠቃሚ ለመሆን እስኪሰባበሩ መሯሯጥና የመሳሰሉ ህገ ወጥ አካሄዶች በተጨባጭ መኖራቸው በግልፅ የሚታዩ ቀላል ማሳያዎች ናቸው

የጠባብነትና የትምክህተኝነት አደጋዎችም በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን እዚህም እዚያም እንዳሉ በተጨባጭ ተረጋግጧል በተግባር ተገልጦ ያየነውና የሰማነውም ይኸው ነው ጠባብ ኦሮሞ እንዳለ ሁሉ ጠባብ ትግሬና የደቡብ ሰው ስለመኖሩ መጠራጠር አያስፈልግም

የትምክህት አመለካከትና ድረጊትም በተለምዶ በዋነኛነት ለአማራ ተወላጆች የተሰጠች ታርጋ ብትሆንም እዚህም እዚያም ትምክህት እንዳለች ይታወቃል አዲሱ አደጋ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ደግሞ ለተወሰኑ ቡድኖች የተሰጠ ስያሜ ነው ማለት ይቻላል የአክራሪነትና ሽብርተኝነት ሰፈር ሰዎችም የራሳቸው ፍላጎት ያላቸው ስለሆኑ ከውስጥም ከውጭም ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚሯሯጡ ስለመሆናቸው በተግባር ተረጋግጧል

እንግዲህ አነዚህ አሳሳቢ የሆኑ ተጨባጭ አደጋዎች በኢትዮጵያችን ላይ በማንዣበብ ላይ እያሉ ምንም የማይሞቃቸውና የማይቀዘቅዛው ባለስልጣን እንዳሉ እየተሰተዋለ ነው ባለፈው መስከረም ወር 2008 ላይ መልካም አስተዳደርን የማረጋገጥ ንቅናቄ በይፋ ከታወጀ ወዲህ የከፍተኛ ባላስልጣኖች ሰፈር አልነካህም አትንካኝ በሚል የተማማሉበት ይስላል

እውነት ነው ከታችኛው እርከን ላይ ህዝብ እንዲጉላላ ያደረጉና የግለኝነት በሽታ ይዟቸው ሲሰቃዩ በቆዩ የተወሰኑ ሰዎች ላይ ይነስም ይብዛ አስተማሪ ሊሆን የሚችል የእርምት እርምጃ ተወስዷል ይህም ቢሆን ህዝብ ላይ ሲደርስ ከቆየው እንግልት ጋር ሲነፃፀር ምንም እንዳለሆነ እየተነገረ ነው
“የዓሳ ምኑ ከአናቱ” እንዲሉ ከላይ ያለው ቁንጮ ባለስልጣን በአግባቡ ራሱን በመፈተሸና በመፈታተሽ ንፅህናውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል አልነካህም አትንካኝ ብሎ መማማል የትም አያደርስም


የታችኛውም ቀሪ አካል በህብረተሰብ፤በድርጅትና በመንግስት ውስጥ የሚገኘው ሌላው ላይ ጣቱን ከመቀሰሩ በፊት ራሱም በአደጋነት ከተፈረጁት ጉዳዮች ጋር  ከተያያዙ መሰናክሎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ንፁህ ሳይሆኑ በሌላው ላይ እያጓሩ ንፁህ ለመምሰል መሯሯጥ መጨረሻው አያምርም በህዝብ ዘንድም አስተሳሳቢ ነውና ልብ ይሏል

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa