አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የብሄራዊ አትሌቲክስ ቡድን አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
*** ነፍስ ይማር***

ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ጥር 1939 ዓ ም በሰሜን ሸዋ ተጉለት እና ቡልጋ ተወለዱ። ዶ/ርወልደ መስቀል ኮስትሬ በ2 ዙር በመጀመሪያ ከ1964 -1970 እንደገና ደግሞ ከ1974 -1982 በአጠቃላይ 14 አመታትን በወጣትነታቸው ካሳለፉባት የምስራቅ አውሮፓዋ ሀገር ሀንጋሪ በባዮሎጂ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤት ናቸው፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል ወደ ሀንጋሪ ለትምህርት ከማምራታቸው ከሳምንታት በፊት በ1964 በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለሚሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድናችን በ800 ሜ እና 1500 ሜትር ለተወዳዳሪነት ተመርጠው ነበር፡፡ ነገር ግን ትምህርት ይሻለኛል በማለት ውድድሩን በመተው ወደ ሀንጋሪ አምርተዋል፡፡ የአትሌቲክስ አሰልጣኝነትን የጀመሩት በኮተቤ ኮሌጅ አስተማሪ እያሉ በ70ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሲሆን በ1972 የሙኒክ ኦሎምፒክ በሚሳተፈው ቡድናችን ውስጥ ዋና አሰልጣኝ ለነበሩት ንጉሴ ሮባ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ነበር፡፡

ዶክተር ወልደመስቀል በ1982 የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በስፖርት ኮሚሽን ውስጥ በከፍተኛ ባለሙያነት ሰርተዋል፡፡ ወደ አትሌቲክስ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝነት የመጡት የአሰልጣኝ ንጉሴ ሮባን ኅልፈት ተከትሎ በ1992 ነው፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው ምርጥ ምርጥ አትሌቶች ጀርባ እኝህ ኮስታራ አሰልጣኝ ይገኛሉ፡፡ ከ1992 የባርሴሎና እስከ 2008 ቤጂንግ ኦሎምፒክ ለ16 ዓመታት በዘለቀው የዋና አሰልጣኝነት ዘመናቸው ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ያኮሯትን የ5000 እና የ10,000 ሜትር አትሌቶች ለውጤት በማብቃት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድንን እያሰለጠኑ በተሳተፉባቸው አምስት ኦሎምፒኮች ላይ 28 ሜዳሊያዎችን በድምሩ ለሀገራቸው አስገኝተዋል (13 ወርቅ 5የብር እና 10 የነሐስ ሜዳሊያዎችን)፡፡ በአትሌቲክሱ ዓለም ለአሰልጣኞች የሚሸለመውን የዓመቱ ምርጥ የአሰልጣኝነት ሽልማትን በ2006 ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ብሎ ሸልሟቸዋል፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል በስፖርት ዘርፍ የ2007ዓ.ም የበጎ ሠው ሽልማትንም ተቀብለዋል።

ዶ/ር ወልደመስቀል ከአመታት በፊት የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ካደረጉ ቡኃላ ለበርካታ ጊዚያት አልጋ ላይ ውለው የነበረ ሲሆን ግንቦት 07/2008 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa