የሕግ ጥሰት ፈፅሞ ተጠያቂ አለመሆን አይቻልም

ይዋል ይደር እንጂ ማንኛውም ሕገ ወጥ ድርጊት ተጠያቂ ያደርጋል የሕግ ጥሰት በመፈፀም ከተጠያቂነት ያመለጠ ሰውና አካል የለም ነገር ግን ሕገ ወጥ ድርጊት የተፈፀመ ስለመሆኑ እንዳይታወቅ በሚደረገው ጥረት ተጠያቂነት ሊዘገይ ይችላል መቼም ቢሆን ተጠያቂነት ሊቀር እንደማይችል ግን መገንዘብ ጠቃሚ ነው

ለምሳሌ በትንሹ እንይ ብንል  እንኳ ዶክተር ኢንጂነር እያለ በሃሰተኛ የማዕረግ ስም ብዙዎችን ሲያጭበረብር የቆየው ሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳዩ ለሕግ ቀርቦ ሲታይ ከቆየ በኃላ ተጠያቂ በመሆን የእስር ቅጣት ተወስኖበት የቅጣት ጊዜውን በማጠናቀቅ ከእስር እንደተለቀቀ ከሰሞኑ እየተሰማ ነው
መቀጣት ለመታረም ነውና ሳሙኤል ዘሚካኤልም ከስህተቱ ተምሮ መልካም ዜጋ መሆን እንደሚችል አምናለሁ ሌባ ለአመሉ… እንዳይሆን እንጂ

ልክ እንደሳሙኤል ሁሉ ሌላውም ግለሰብ፤መንግስታዊ አካልና ባለስልጣን የሕግ ጥሰት ፈፅሞ ተጠያቂ አለመሆን እንደማይችል በአገራችን ያለው ተመክሮ በማስረጃነት ሊቀርብ ሚችል ነው
ባለፉት አመታት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ብልሹ አሰራሮችን በመጠቀም የሕዝብና የመንግስትን ገንዘብና ንብረት የመዘበሩ ግለሰብ ባለስልጣናት ሕግ ፊት ቀርበው ፍርዳቸውን አግኝተዋል የፍርዳቸውን ቀን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙም እንዳሉ ይታወቃል

ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሰሞኑን ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፣ ብዛት ያላቸው የመንግሥት ተቋማት በተደጋጋሚ በየዓመቱ የሚሰጣቸውን አስተያየት ተግባራዊ በማድረግ ከማሻሻል ይልቅ፣ ወደባሰ ጥፋት እየገቡ መሆናቸውንና ለዚህም ዋና ምክንያቱ ተጠያቂ ያለመደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል


እንግዲህ “አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል” እንዲሉ ኢትዮጵያ ገንዘብና ንብረቱ በተለያዩ ምክንያቶች ተመዝብሮበት ዝም የሚል ሕዝብና መንግስት የላትም ሁሉም ግለኛ በሰበብ አስባቡ የለቃቀማትን ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት መመለሱ አይቀርም ይህም የሚሆነው የህግ የበላይነትን በማስከበር ነው በአገራችን ማንኛውም ሰውና አካል ከሕግ በላይ መሆን የሚችልበት ሁኔታ በፍፁም የለምና

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa