የቀድሞ የሱሉልታ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 14 ግለሰቦች በሙስና ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች - ሜይ 06, 2016 በሱሉልታ ከተማ ከ140 ካሬ ሜትር ጀምሮ በተለያየ መጠን የወልና የመንግስት መሬትን በጥቅም በመመሳጠር ለ7 ሺህ ግለሰቦች ስጥተዋል ተብለው የተጠረጠሩ የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ስዩም ሀይሉን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ዛሬ ፊንፊኔ ዙሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።read more አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች አስተያየቶች
invastimantii Oromiyaa caalmatti cimsuuf qajeelfamni dambii haaraan ba'ee hojiirra ooluu eegaleera - ኤፕሪል 23, 2020 Finfinnee Eebila 15/2012(TW) Sochii misooma invastimantii Oromiyaa caalmatti cimsuuf qajeelfamni dambii haaraan bahee hojitti galameera- Komishiinara komishiinii Invastimantii naannoo Oromiyaa Obbo Hayluu Jaldee. Sochii misooma invastimantii bu’a qabeessa ta’e lafa qabsiisuuf qajeelfama danbii haaraa boordiin mirkanaa’ee hojitti galamuu isaa obbo Hayluu Jaldee ibsa guyyaa har’aa miidiyaaleef kennaniin ibsaniiru. Dambiin haaraan kun karaa Qonnaan bulaa fi Horsiisee bulaa fayyadamaa taasisuu da nda’uun tumamuu isaa kan dubbatan Obbo Hayluu Abbootii qabeenyaa sadarkaan jiran hojitti galchuu keessattis xiyyeefannoon kan itti kenname ta’uu dubataniiru.Qajeelfama kana keessatti facaatii tajaajiltummaa seektaroota gara garaa keessatti argaman gara tokkotti fiduun tajaajila iddoo tokkoo akka argataniiif haala kan mijeessudha jedhan. Qonnaan Bulaa fi Horsiisee Bulaa karaa liizii fi kiraa irraa bilisa ta’een gara invastimantiitti galchuu fi Lafti Qonnaan bulaa invastima... ተጨማሪ ያንብቡ
የዶ/ር ነጋሶ “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” መፅሐፍ - ሜይ 02, 2016 አንጋፋው የታሪክ ምሁርና ፖለቲከኛ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የፃፉትና በአዳዲስ የምርምር ውጤቶች ላይ ተመስርቶ እንደተዘጋጀ የተነገረለት “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” የተሰኘ አዲስ መፅሃፍ ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ መፅሃፉ የኦሮሞ ህዝብ አመጣጥ ታሪክ ላይ ከዚህ ቀደም የሚታወቁ እውነታዎችን የሚሞግት ሲሆን የኦሮሞ ታሪክ በኢትዮጵያ የሚጀምረው በ16ኛው ክ/ዘመን እንደሆነ ሲገለፅ የቆየው የተሳሳተ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ማስተማሪያ መፃህፍት ላይ ሳይቀር የኦሮሞ ህዝብ በ16ኛው ክ/ዘመን መነሻውን ከባሌ መደወላቡ አድርጎ ወደ ሰሜን መስፋፋቱ ተተርኳል የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ የኦሮሞ ህዝብ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በፊት፣ ከላሊበላ የስልጣኔ ዘመን ጀምሮ በሰሜኑና መካከለኛው የሀገሪቱ ክልል የኖረ ህዝብ ነው፤ ብለዋል፡፡ ማህበረሰቡ ከሰሜን ወደ ደቡብ የተስፋፋ እንጂ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተስፋፋ አለመሆኑን ዶ/ር ነጋሶ በመጽሐፋቸው ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ሲማሩ፣ መምህራቸው ፕ/ር ዶ/ር ታደሰ ታምራት፤ “የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖትና የክርስቲያን ዐፄ አገዛዝ ወደ ደቡብ መስፋፋት” የሚለውን የታሪክ ክፍል ሲያስተምሯቸው፣ በ13ኛው ክ/ዘመን በሰሜን ሸዋ ገላና እና ያያ የሚባሉ ህዝቦች ቆርኬ ለሚባል አምላክ ይሰግዱ እንደነበር የነገሯቸውን መሰረት አድርገው ምርምር ማካሄዳቸውን ዶ/ር ነጋሶ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በመፅሃፉ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ጎሳዎችን የትውልድ ሀረግ ቆጠራዎች እንዲሁም፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን በማጣቀስ፣ የኦሮሞ ህዝብ ፍሰት ከሰሜን ወደ ደቡብ እንደነበር ምሁሩ ማሳየታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በተለይ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ያለው መስተጋብር በመጽሐፋቸው መዳሰሱ... ተጨማሪ ያንብቡ
ቤተ መንግሥት ድረስ ገብተው ጉድ ሊሰሩን የነበሩ የሠራዊቱ አባላት መኖራቸውን ካሰብን...... - ጃንዋሪ 10, 2019 ቤተ መንግሥት ድረስ ገብተው ጉድ ሊሰሩን የነበሩ የሠራዊቱ አባላት መኖራቸውን ካሰብን፤ በሕዝብ ላይ ተኩሶ ሀገር ወደ ትርምስ የሚከት አምስትም አስርም የሠራዊት አባል እንደሚኖር አስበን፤ በሥርዓት ስለማሸነፍ እናስብ፤ በመተማ የተፈጸመው ድርጊት የሚኮነን ነው፡፡ መተኮስን እንደ አማራጭ ማየት አልፈልግም በሚል መከላከያ ሠራዊታችን ውስጥ ዛሬም ቃታ ስበው ሀገር ማተራመስ የሚፈልጉ ድብቅ ዓላማ ያላቸው አባላት እንዳሉ አሳይቶናል፡፡ መፍትሔው ግን ተረጋግተን ማሰብ ነው፡፡ ተረጋግተን መጠየቅ ነው፡፡ ተረጋግተን ማሸነፍ ነው፡፡ በቅርቡ ወደ ቤተ መንግሥት ገስግሰው ጠቅላዩን ለመጠቅለል ያሰቡ የሠራዊቱ አባላት በጦር ፍርድ ቤቱ የተፈረደባቸውን ሰምተናል፡፡ ቤተ መንግሥት ድረስ ሄዶ እድሉን መሞከር የሚፈልግ የሠራዊት አባል ካለ ህዝብ ማሃል ሆኖ የሚያበጣብጥ ነገር ቢፈ ጽም አይገረመን፡፡ ይልቁንስ ሁሌም ንቁ ሆነን ችግሩ ብሶ እንዳይጎዳን እንተባበር፡፡ የመተማን ችግር በተመለከተ አማራ ብዙሃን በዘገበው ዘገባ ላይ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ የሱር መኪኖች ተፈትሸው እንዲወጡ በነበረው ስምምነት ከህዝቡ ጋር እየተካሄደ ያለው ውይይት ሳያልቅ መኪኖቹ በመውጣታቸው ለማስቆም በፈለጉት ሰዎች እና በመከላከያ መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን በአካባቢው በድብቅ ሲፈጽመው የኖረው ሴራ እንዲህ ባሉ ወገን የሚረግፍባቸው ግጭቶች መንስኤም መሆኑ ያሳዝናል፡፡ የህግ አለመከበር ችግር ውሎ አድሮ አሁንም በሱር ምክንያት ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ አሁንም በሱር ምክንያት መተማ ለብጥብጥ ተዳርጋለች፡፡ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥም ግን ተረጋግቶ መፍትሔ መፈለግና መደማመጥ ያስፈልገናል፡፡ ቀጠናው መከላከያ ይውጣ የሚባልበት ቀጠና አይደለም፡፡ የተቀ... ተጨማሪ ያንብቡ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ