የኪራይ ሰብሳቢ ኃይሎች የበላይነት

በአገራችን ኪራይ ሰብሳቢነት አደገኛ የጥፋት መንገድ እንደሆነ የሚያረጋግጡ አብነቶችን ለማቅረብ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም ያስቸገራል ቢባል እንኳ ኪራይ ሰብሳቢነት ሕብረተሰብን ምን ያህል እንደሚያመሰቃቅል ከብዙ የአለማችን የከሸፉ መንግስታት ታሪክ በመነሳት ማረጋገጥ ይቻላል ሁለቱንም የታሪክ ማስረጃዎች  በማጣቀስ የኪራይ ሰብሳቢነትን ውጤት እንመልከት ከተባለ  በአገራችን ኪራይ ሰብሳቢነት መንግስታዊ ስልጣን ይዞ የነበረበትን የደርግ ስርዓት  ዋቢ ማድረግ ይቻላል 

ደርግ ስልጣን ላይ ሲወጣ ይህ ነው የሚባል ሃብት ያልነበራቸው ወታደሮች ስልጣናቸውን በመጠቀም  ያልወረሱት የዜጎች ሃብት አልነበረም ቤቶችን፣ፋብሪካዎችን፣ባንኮችን፤ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንዲሁም መሬትን ወርሰዋል በዚህም ሳይወሰኑ ከእነሱ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሃብት በማፍራትና  በማበራከት ተግባር ውስጥ እንዳይገባ ከልክለዋል

ይህ በተግባር ይተረጎም ይችል የነበረው የሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብት ሲታፈን በመሆኑ ዴሞከራሲን ረግጠዋል የብሄሮችን ህልውና ክደው አሃዳዊ መንግስት እንደተጫነባቸው እንዲቀጥል አድርገዋል ነገር ግን ይህን በማድረጋቸው ለውጥ ፈላጊ የሆነውን የአገራችን ሕዝብ ተቃውሞ ቀስቅሰዋል በዚህ ምክንያት ለአስራ ሰባት ዓመታት  የተቀጣጠለው ጦርነት  አገሪቱን ከሞላ ጎደል የውድቀትና የመበታተን አፋፍ ላይ አድርሷት ነበር ይህ ኪራይ ሰብሳቢነት ለመንግስታዊ ስልጣን  ሲበቃ በማይቀር ሁኔታ የሚከሰት ውጤት  እንደሆነ የሚያረጋግጥ የራሳችን አገር ተመክሮ ነው


በሌላ በኩል በሶማሊያ፤በሊቢያ፤በቡሩንዲ፤በደቡብ ሱዳን፤በኤርትራና  በመሳሰሉት የተከሰቱት የከሸፉና በመክሸፍ አቅጣጫ የሚጓዙ መንግስታት እዚሁ በቅርባችን የኪራይ ሰብሳቢነት የበላይነት ከሰፈነባቸው ስርዓቶች ጋር  ተያይዞ የሚመጣው ውጤት ምን እንደሆነ የሚያሳዩ አብነቶች ናቸው በላቲን አሜሪካና በአፍሪካ በእስያና  በመካከለኛው ምስራቅ የታዩ የመንግስታት መቃወሶችም  በዋነኛነት ከኪራይ ሰብሳቢነት የበላይነት ጋር የተያያዙ ናቸው


ኪራይ ሰብሳቢ ኃይሎች የበላይነት በሚይዙበት ጊዜ ሁሉ በየአገሩ የማፍያና መሰል ኃይሎች ልዕልና የተረጋገጠበትና አገራቱ የወንጀል መነኻሪያዎች እስከመሆን እንዲደርሱ ያደረገ ነው በሰው ልጆች ላይ የሚካሄድ ንግድ የሚደራበት ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር የሚስፋፋበት የአደንዛዥ ዕፆች ዝውውርና የወሲብ ንግድ የሚስፋፋበት ከዚህም አልፎ አሸባሪነትና አክራሪነት እየተመጋገቡ አገርና ሕዝብ የሚያጠፉበት በአጠቃላይ ደግሞ ብዙሃኑ ሕዝብ ለከፋ ጉዳት የሚጋለጥበት ሁኔታ ይፈጠራል ( አዲስ ራዕይ 11ኛ ዓመት ቅፅ 5 ቁጥር 4)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman