የጠባቦቹና ትምክህተኞቹ ትውከት ሲቀጥል

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር በአንድ ወቅት በሰጡት ይፋዊ መግለጫ “ጠባብና ትምክህተኛ    ኃይሎች አርፈው እንደማይቀመጡ ስለምናውቅ እኛም ስራችንን ጠንክረን እንሰራለን’’ ብለው ነበር።


ነበር ነው ያልኩት አሁን አይደለም የተናገሩት።እናማ ጠባቦቹና ትምክህተኞቹ አጀንዳ ቢሶች አጀንዳ ፈጥረናል ብለው በየጊዜው የሚቀባጥሯቸው ነገሮች እነዚህ ኃይሎች ተስፋ የቆረጡ መሆናቸውን ያሳያል።

ከሰሞኑ ደግሞ ትኩረታቸው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር በአቶ በከር ሻሌ መተካት ላይ አትኩረዋል።

ቀደም ሲል አቶ በረከት ስምኦን ላይ በማትኮር አንዴ በጠና ታመዋል፤አንዴ ደግሞ ሞተዋል ሲሉ የውሸት ፕሮፓጋንዳቸውንና ትውኪያቸውን በማህበራዊ ድረ ገፆች ሰረጩ የቆዩት እነዚህ ሀገር ካህዲ ኃይሎች የሞኑ ትኩረታቸው ደግሞ በአሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ሆኗል።

ክቡር አቶ ሙክታር ከድር ከሕዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ ነው በአቶ በከር ሻሌ ተተክተዋl እሳቸው ወደ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር እንዲመለሱ ተደርጓል በማለት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ላይ የምትገኙ ኃይሎች በእኩይና አሳፋሪ ተግባራችሁ እፈሩ።
አቶ ሙክታር በጠና ታመው ባንኮክ ታይላንድ በመታከም ላይ ላይ ናቸው የሚል ትውከትም ነበረ ሰሞኑን።በዚህም ለአቶ ሙክታር የአቶ አለማየሁ አቶምሳ እጣ ደርሷቸዋል ብሎ  የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መራሯጥ አስተዛዛቢ ነው።


በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተሰረዘው ማስተር ፕላን ሽፋን ተቀስቅሶ የነበረው ሁከት ሙሉ በሙሉ ተወgiዶ የቀድሞው ሰላማዊ ሁኔታ በመቀጠል ላይ እንዳለ  ግጭቱ እስከ አሁን ቀጥሏል በማለት የግል ፍላጎትን ለማሳካት መፍጨርጨር የትም አያደርስም።

ይህን በመፈፀም ላይ የሚገኘው ፅንፈኛው ጀዋር መሃመድ፤የፌስ ቡክ ሰራዊቱና የትምክህተኛው ኃይል ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ለነገሩ በተፃፈና በተሰማ ነገር ሁሉ የማመን በሽታ የተያዙ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን እነዚህ ኃይሎች ስለሚያውቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ የሚያሰራጩት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተቀባይነት ያገኝልናል በሚል ከንቱ ተስፋ እስከ አሁን በመናወዝ  ላይ ይገኛሉ።በቀጣይ የሚመጣው ትውከታቸው ምን ይሆን?




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman