ትክክለኛው የፀረ ሽብር ሕጉ ተግባራዊነት ወቅት አሁን ነው

ሰዎች በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በሰላም መግባት አለባቸው!ፍላጎታቸውም ይኽው ነው ለሽብርተኞችና አከራሪዎች ፍላጎት ስኬት ሲባል ሕዝቦች መሸበር የለባቸውም።ሰላም ልማትና ዴሞክራሲያችን ያለ ምንም ማቅማማት  ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።


ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን ከሕዝቦች የተሰጠውን ሃገር የማስተዳደር ታላቅ ኃላፊነት ያለ ምንም መሸፋፈንና መልፈስፈስ መወጣት ይጠበቅበታል።

ሕዝቦች ኢህአዴግን የመረጡት ሰላምና ልማቴን ያስቀጥላል፤ዴሞክራሲያዊ መበቶቼን ያስከብራል ብለው እንጂ በማንም ተልካሻ አላማ ቢስ አክራሪና ፅንፈኞች ውድ ህይወታቸውን ለማጣት አይደለም።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በማስተር ፕላን ሽፋን በተነሳው ብጥብጥ ምክንያት የውድ ወገኖቻችን ሕይወት ጠፍቶ በቁጭትና በሃዘን ላይ ባለንበት ወቅት በሌሎች አካባቢዎችም የሰዎች ሕይወት የሚቀጠፍበት ምክንያት ግልፅ አይደለም አሳዛኝ ነው።

ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በእምነት ምክንያት እንዲቃቃሩ የአገራችን ሰላማዊ ሁኔታ ፈሩን እንዲስት የከሰሩ አክራሪዎች፤ኪራይ ሰብሳቢዎች፤ጠባቦችና ትምክህተኞች ተቀናጅተው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

ለመሆኑ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ የሚደረግበት የጦር ማሳሪያ ምንጩ ከወዴት ነው?ሕዝቡስ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሰላሙን የማስከበር ኃላፊነት የለበትም?ምን እስኪሆን ነው የሚጠበቀው?

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች በስጋት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ተስተጓጉለው ቆይተዋል።የምንገኘው በድርቅ አደጋ ላይ ነው።የውስጥ ኪራይ ሰብሳቢው ላለመነካት አድፍጦ በመጠበቅ ላይ ያለ ይመስላል።ጠላቶቻችን በዚህ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ላይ መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።በጋምቤላ የግለሰቦች ፀብ ተስፋፍቶ ወደ ብሄረሰቦች የሚዛመትበት ምክንያት ምንድነው?

የአገራችን የፀጥታ ኃይሎች ከራሳችን ተርፈው ለሌሎች አገራትም  ሰላም መከበር  ከፍተኛ አስተዋኦ እያበረከቱ ባሉበት ወቅት እኛ በሰላም  ለመኖር ዋስትና ወደ ማጣት ሁኔታ እየተጉዋዝን ነው?

ዜጎች ሰላም አጥተው በስጋት በመኖር ከልማትና እድገት እንቅስቀሴ ላይ መገታት የለባቸውም።ለማንኛውም በብዙ ኃይሎች ፍላጎት ምክንያት ያለንበት ሁኔታ ምቹ አይመስልም፤ያንዣበበው አደጋ በእንጭጩ እንዲቀጭና የህዳሴ ጉዞአችን እንዳይደናቀፍ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፤ሕዝቦች ከመንግስት ጋር ይተባበሩ ዴሞክራሲያዊ ጎዞአችን በማይደናቀፍበት ሁኔታ አጥፊዎች ይቀጡ፤ለሕግ ይቅረቡ  አስቸኳይ ውሳኔ ይሰጣቸው የፀረ ሽብር ሕጉም በአግባቡ ተግባራዊ ይሁን።ሰላም ለውድ አገራችን ኢትዮጵያ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman