25 ሚሊየን ብር ለባለስልጣን መኖሪያ ቤት?????



መስከረም ሳይጠባ ጉድ አይሰማም እንዲሉ ከሰሞኑ አንድ ጉድ ጉድ የሚያስብል ነገር ተሰምቷል።ጉዳዩ የከተማ አጀንዳ ሆኖም ሰንብቷል፤በስልጣን ዘመን ቆይታው ሕዝብን ሲያገለግል ለቆየ ባለስልጣን ደረጃው የተጠበቀ መኖሪያ ቤት እየተገነባ ነው ሲል አንዱ የስራ ኃላፊ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ሰሞኑን የሰጠው መረጃ እውነትም አስደማሚ ነው።


ሰውዬው ለባለስልጣናት ደረጃው የተጠበቀ ቤት አንዲገነባ ሕጉም ያዛል፤በዚሁ መሰረት በአንዱ የአዲስ አበባ አካባቢ  ለባለስልጣናት ደረጃቸው የተጠበቁ መኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ ሲል በመኩራራት መግለጫ ይሰጣል፤የሸገሩ  ዘጋቢም ሰውዬው የሚሉትን ያሰማል  ለምን? በምን ምክንያት?በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?በማለት መጠየቅ ያልቻለው የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ማህበራዊ ኃላፊነት የማይሰማው ስራውን ከውኖ ቁጭ አለ።ሸገር ይህን መረጃ ማቅረብ አልነበረበትም የሚል አቋም የለኝም፤ተገቢ ያልሆነው የቀረበበት ሁኔታ ነው።

ጉዳዩ  አሁንም አጀንዳ ሆኖ እንደቀጠለ አለ።በማህበራዊ ድረ ገፆች የመወያያ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው ይህ የመንግስት ባለስልጣናት መኖሪያ ቤት ግንባታ ጉዳይ በቂ ማብራሪያ የሚያስፈልገው እንደሆነ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ግልፅ ሁኔታ ያስረዳል።እኔ ነኝ ያለ አሳማኝ መግለጫ ይስጥ።

የሆነስ ሆኖ ይህ ጉዳይ አሳሳቢው በሆነው የድርቅ አደጋ ላይ ባለንበት በአሁኑ ወቅት ሊፈፀም የታሰበበት ምክንያት ምንድነው?የአገራችን ባለስልጣናት በስልጣን ወቅት ቆይታቸው ወጥተው ወርደው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነት ለሰጡት አገልገሎት ክብርና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል፤በሽምግልና እድሜያቸው ወቅትም ተገቢውና አስፈላጊው እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል።ነገር ግን በዚህ አይነት ሁኔታ መሆን ያለበት አይደለም፤አይገባምም።መዋኛ ምናምን የተሟላለት የተባለው መኖሪያ ቤትም ለባለስለጣናቱ እድሜ አይጨምርም።ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታና የእድገት ደረጃ፤እንዲሁም ከአገሪቱ ዜጎች አኗኗር ብዙም ያልራቀ እንክብካቤ ብቻ ነው ሚያስፈልጋቸው።

ሕግ እንዲወጣ የተደረገው በሰው ነው፤ሕግ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ከሆነም የሚሻሻል እንደሆነ ይታወቃል።ስለዚህ ሕጉም ያዛል በሚል ድፍን ያለ ምክንያት ብቻ መከራከር አዋጭ አይደለም።

አገራችን ከድህነት ወጥታ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ተሻሽሎ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአለም አገራት ጎን ለመሰለፍ በጉጉት ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲባል ይህን መሰል አስተዛዛቢና ባለ ስለጣናቱንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ማንም ይሁን ማን የሚያስጠይቅ ሊሆን ይገባል።

የኢህአዴግ መራሹ ልማታዊ መንግስታችን ስም በብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የተወደሰውን ያህል ለአደጋ የተጋለጠ እንዳይሆንም ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ለኢትዮጵያ ሕዳሴ ቀጣይነት ፍላጎትና ቁርጠኝነት ካለው ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa