ብአዴን ሰላምና ዲሞክራሲን በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነትን አረጋግጧል - የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ



የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ባለፉት አመታት የሰላምና የዲሞክራሲ ስርአትን በመገንባት የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጡን የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ።


ማእከላዊ ኮሚቴው የድርጅቱን 35 የምስረታ በአል አስመልክቶ ባወጣው የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ የዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብና ተግባር መሰረት እንዲይዝ ያስቻለ መሆኑንም አመልክቷል።

በመግለጫው በህዝብ ተሳትፎ የላቀ ዕድገትና ትራስፎርሜሽን ለማረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግም ነው ይፋ ያደረገው።

የተጀመረው የለውጥ ጉዞው የተሳለጠ እንዲሆን ኪራይ ሰብሳቢነትን፣ ኋላቀር አስተሳሰቦችንና ተግባራትን ለማስወገድ የላቀ ትግል ማድረግ እንደሚገባም ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው አስገንዝቧል።

የአየር ንብረት መዛባትን በመቋቋም የግብርና ልማትን ለማሳደግ ለመስኖና ለእርጥበት እቀባ ትኩረት እንደሚሰጥ መግለጫው አመልክቶ፤ በአምራች የኢንዱስትሪ ዘርፍ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የላቀ ጥረት እንደሚካሄድ ገልጿል።


በተያያዘ የብአዴን 35 የምስረታ በአል በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ቀጥሏል።

በአማራ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ በአንጋፋ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች በተዘጋጀ መድረክ ላይ ድርጅቱ ከተመሰረተበት ወቅት አንስቶ እስካሁን ያካሄደውን የትግል ጉዞ የሚዘክር የኪነጥበብ ዝግጅትና ታሪካዊ ሙዚቃዊ ቲያትር ለታዳሚዎች ቀርቧል።


በሙሉአለም አዳራሽ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮችና የድርጅቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉበት የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

በፓናሉ ላይ የድርጅቱን 35 አመታት ታሪክ የያዘ መፅሀፍ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የድርጅቱ ሊቀመንበር በሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ተመርቋል።


የብአዴን 35 አመትና የጥረት 20 አመት የምስረታ በአል በማስመልከት የተሰራ ሀውልትም ተመርቋል፡፡

ሀውልቱ የክልሉን አርማና ሶስቱን የመንግስት መዋቅሮች ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚውን አካላት የሚያሳይና ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን የሚጨምር እንደሆነ ተገልጿል።
በክልሉ የሚገኙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በባህርዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር የሰልፍ ትርኢት አሳይተዋል።


በአሉ ዛሬም በተለያዩ ህዝባዊ ንቅናቄዎች፣ የፓናል ውይይቶችና የኪነጥበብ መርሃ ግብሮች መከበሩን የሚቀጥል ሲሆን፥ በነገው እለት በባህርዳር ስታዲየም በሚደረግ ዝግጅት ይጠናቃቀል።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa