ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በተጨማሪነት በግድያ ወንጀል መጠርጠሩን ገለጸ



መምህር ግርማ ወንድሙ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል የተፈቀደው ዋስትና ላይ የመርማሪ ፖሊስ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ።


የአዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ከተጠርጣሪው ቤት ያገኘሁት ስምንት ሲም ካርድ ላይ እንዲጣራ ለኢትዮ ቴሌኮም ልኬ ውጤት እየጠበኩ ነው፤ ሌላ ተጠርጣሪም ስላለ ያን ለመያዝ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ቢልም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠየቀው የምርመራ ስራ ተጠርጣሪውን ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም በማለት ዋስትና መፍቀዱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ጠይቆ ዋስትናውን በማሳገድ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ተከራክሯል።

ችሎቱ የሁለቱን ወገን ክርክር መርምሮ ፖሊስ የተሰጠው ጊዜ በቂ ነው፤ ቀሪ ምርመራውን ለማድረግም ተጠርጣሪውን ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም ሲል የተፈቀደውን ዋስትና አጽንቶታል።

በዚህም መምህር ግርማ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል 50 ሺህ ብር፣ በሀሰተኛ ሰነድ በመገልገል ደግሞ 40 ሺህ ብር በጠቅላላው 90 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቅዶላቸዋል።

በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን መምህር ግርማ መንድሙን ከዚህ በፊት ከተጠረጠሩበት ወንጀል በተጨማሪ በግድያ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ሲል አመልክቷል።

የምርመራ ቡድኑ ጉዳዩን ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ያመለከተ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠረጠረበትን የግድያ ወንጀል ዝርዝር እና የምርመራ ሂደቱን ለችሎቱ እንዲያቀርብ ለህዳር 20 ቀን 2008 . ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ከፖሊስ ባገኘነው መረጃ መሰረት መምህር ግርማ ወንድሙ እስከ ህዳር 20 2008 . ድረስ በእስር የሚቆዩ ይሆናል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa