የአሸባሪው ቡድን መሳሪያ ኡኡታ
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያችን ስኬት ያንገበገባቸው፤ክፉዋን
እንጂ መልካሟን ነገር በፍፁም መስማት የማይሹ የድርቅ አደጋ ስለተከሰተም በጣም ደስ ያላቸው ቡድኖች በአገር ውስጥም በውጭ አገራትም
እንዳሉ ይታወቃል።ምቀኛ አታሳጣኝ አለ ያገሬ ሰው።
በአገራችን ስኬታማ መሆን አይናቸው ቀልቶ ደም
የሚለብስባቸው፤እርዳታ የሚያካላክሉ፤በፕሮፓጋንዳቸው አገር በመቃጠል ላይ እንዳለች አስመስለው ሌት ተቀን ቱሪናፋቸውን የሚነፉ ትምክህተኛና
ጠባብ ኃይሎች ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ላይ ይገኛሉ።
መቼም ይህን አታውቁም ብዬ አይደለም ይህን
የምፅፈው።ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ከሰሰሞኑ አንዱ አርቲስት ተብዬ ሰው በአገራችን ከሚገኙ ቱባ ባለስልጣናት ጎን ፎቶግራፌን
ለጥፎ ክሊፕ መስራቱን ተመለከትኩና ነገሩ ትንሽ ገረመኝ።
ግለሰቡ አራርሳ ገቢሳ ይባላል፤ያው እነዚያው
ፅንፈኛ ጠባቦች ገጥመው የሰጡትን የሚያነበንብ መሆኑን መገንዘብ አይከብድም።ሰዎችን በማጣጣል በክሊፑ የሚያነሳው ይህ ሰው የኦሮሞ ሕዝብ
ይጠይቃችኋል የሚል መልዕክት ያለው ንብነባውን ያነበንባል።
የኦሮሞ ሕዝብማ ማን ለእርሱ እንደቆመ በደንብ
ያውቃል።ጠባቡና ትምክህተኛው ኃይል መቼም ቢሆን ለእርሱ እንደማይበጅ ከማንም በላይ ይረዳል።
በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሸሸጉትም ሆኑ
በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ጠባብና ትምክህተኞች ምንም ጥቅም እንደማያስገኙለት ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ያውቃል።
የኢሳት ውላጅና ግልባጭ የሆነውና በጀዋር መሃመድ
እየተመራ ያለው OMN አሁን በትክክል የኦነግ ቴለቪዥን ስርጭት መሆኑ ታውቋል።ኦሮሚያ ነጋ ጠባ በመንደድ ላይ መሆኗን በመዘገብ
ላይ የሚገኘው ይህ የጠባቡ ኃይል ሚዲያ በጣም የወረደ ከመሆኑ የተነሳ ልክ የሚያስገባውን ሕዝብና መንግስት በመሸሽ መቀመጫውን በውጭ አገር
አድርጎ ጀግና መሆኑን ይነግረናል።
የነጋ ጠባ ኡኡታው አሁን ወደ ግለሰቦች ወርዷል
የዘፈን ክሊፕ በማሰራት ላይም ይገኛል፤አይ ጥበት።ከአፍ እስከ አፍንጫ ብቻ ማሰብ የሚችለው አእምሮአቸው ይኽው እስከዚህ ድረስ ነው።
አራርሳ ገቢሳ ምን ብሎ እንዳዜመ አድምጡት እስኪ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ