የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ራሱን አገለለ



የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ወጣቱ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን አስታወቀ፡፡


ማክሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2008 .. አመሻሽ ላይ በፌስቡክ ገጹ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን፣ ከአሁን በኋላ የሚወክለው የፖለቲካ ድርጅት እንደሌለና የሚወክለው ራሱን ብቻ እንደሚሆን ገልጿል፡፡

‹‹ከአሁን በኋላ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን የማልወክል እንደሆነ አሳውቃለሁ፡፡ የእኔ ውክልና ለራሴ ብቻ ነው፤›› ይላል በአቶ ዮናታን ፌስቡክ ገጽ ላይ የሠፈረው ማሳሰቢያ፡፡ 

እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ምክንያት ያልገለጸ ሲሆን፣ ሪፖርተር ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ ከራሱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረትም አልተሳካም፡፡ 

አቶ ዮናታን የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ምሩቅና 27 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ከመቀላቀሉ በፊት በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በምርጫ 2007 ወቅት ፓርቲውን ወክሎ በአዲስ አበባ ከተማ በምርጫ ክልል 17 መወዳደሩ ይታወሳል፡፡ አቶ ዮናታን ራሱን ከፓርቲ ፖለቲካ ማግለሉን ውሳኔውን ካስታወቀ በኋላ፣ በፌስቡክ ተከታዮቹ የተሰጡት አስተያየቶች የተደበላለቁ ስሜቶችን አንፀባርቀዋል፡፡   

Source: ሪፖርተር

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa