የኤርሚያስ ውሽከታዎች



የኤርሚያስ ለገሰ ውሽከታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።አዲስ አበባ ባለቤት አልባ ከተማ ሲል  አሉባልታዎችን አጠራቅሞ  አንድ ቅራቅንቦ ነገር ካሳተመ ወዲህ በፅንፈኛ ኃይሎች ሚዲያ ተክቦ በመቅረብ በተለያዩ ወቅቶች በሰጣቸው ቃለ መጠይቆች ታላቅ ሰው የመሰለው ይህ ከሃዲ ሰው እያደር እየቀለለ መሆኑን በተግባር እያሳየን ነው።


ኤርሚያስ ከሰሞኑ ደግሞ ውጭ በሚገኙ በቀድሞ አምባገነን ስርዓት ርዝራዥ ሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ በእነርሱም ትዝብት ስር መውደቁን በሚያሳብቅ ሁኔታ ተንታኝ መሆኑን በማስመሰል ራሱን ለማሳየት ሞክሯል

ይህን ከሃዲ ሰው ለማታውቁት ወገኖቼ ግንዛቤ እንዲያግዝ፤ ኤርሚያስ ለገሰ ማለት ወደ ውጭ አገር ኮብልሎ የጠባቦቹንና የትምክህተኞቹን ካምፕ ከመቀላቀሉ በፊት በኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ ሆኖ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተመድቦ ያገለገለና ወደ ውጭ እስከ ፈረጠጠበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ሆኖ የሰራ ነው።

“የመለስ ቱርፋቶች ባለቤት አልባ ከተማ”በሚል ርዕስ በሃሜት የተሞላ መጽሓፍ ፅፏል፤መፅሃፉ እንኳ መፅሃፍ ሊባል የሚችል ሳይሆን  ከዚህም ከዚያም  የተሰበሰበ የሃሜቶች ጥቅም ነው።

ምናልባት መፅሃፍ ተብዬውን የሃሜቶች ጥርቅም አግኝታችሁ በሚዘናዊ አዕምሮ ያነበባችሁ ወገኖች ይህን ሳትታዘቡ እንደማትቀሩ እርግጠኛ ነኝ።

ይህ ሰው እንደለመደው ከሰሞኑ በአሸባሪው ቡድን ግንቦት ሰባት ሚዲያ ላይ በድሮ የአመባገነን ርዝራዥ ጨርጫሳ ሽማግሌዎች ፊት ቀርቦ ራሱን አዋቂ አድርጎ የኢህአዴግን ጓዳጎድጓዳ የሚያውቅ ይመስል ዲሪቶ አመለካከቱን ይዞ በተንታኝነት መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን አምናለሁ። 

ኤርሚያስ የኢህአዴግን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ለመተቸት ምንም ብቃት የሌለው ደካማ ሰው መሆኑንና የግንቦት ሰባት ቡድን አመራሮችን ለማስደሰት ሲል የባጥ የቆጡን ሲቀባጥር ቆይቷል።የትምህርት ፖሊሲውን ጨምሮ ሁሉንም የኢህአዴግ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በማጥላላት እየተቸ የሚገኘው ይህ ሰው እነርሱ ጋ ሆኖ ማለት ያለበትን ነው እያለ ያለው እንጂ የኢህአዴግ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በተሟላ ሁኔታ በአግባቡ ባለመተግበራቸው ምክንያት የአፈፃፀም ችግር ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ክፍተት እንደሌላቸው ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች አልፎ የአለም ህብረተሰብም ስለ ትክክለኛነታቸው በተመዘገቡት ለውጦች  መነሻነት በግልፅ እየሰመከረ ነው።በተጨባጭም ውጤታማ ስለመሆናቸው በተግባር እየታየ ነው።


የኢህአዴግ ምርጥ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች ልክ እንደ ቀድሞቹ አመታት በአምስተኛው አጠቃላይ ምርጫም ምንጊዜም ለብዙሃን ወገንተኝነቱን በተግባር በማሳየት የሚታወቀው ኢህአዴግ በከፍተኛ የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ድጋፍ እንዲመረጥ አድርጓል።

ኤርሚያስንና ሌሎች ትምክህተኛና ጠባብ ኃይሎችን በአሁኑ ወቅት ልክ እንደ አበደ ውሻ በማክለፍለፍ ላይ የሚገኘው ይኽው ወጤታማ ጉዞ እንደሆነ ግልፅ ነው።

ከአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዲሪቶ አስተሳሰብ በተቃራኒ በመቆም ይህን የሰላ ሂስ በማቅረቤ አንዳንድ ጥቂት ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ጠባብና ትምክህተግለሰቦች እንደሚሰድቡኝና እርግማናቸውን እንደሚደረድሩ አውቃለሁ።

እንግዲህ   ይህን ፅያለ።በዚህ ውኤርያስየግንቦት ሰባት ጀዎች እንደምትቀየሙኝ ውቅም የማምነውን ከማለት ወደ ላ እማልል ይኽው በተግባር አኋችሁ።

ኃይል እንዲህ የምትፍጨረጨረው ለያምው በአማርኛ የምትጽፈው ኔ ስልጣን እንዲሰጥህ ነው ብኛል።ተወደደም ተጠላም የምከትባት ነገር እየተነበበች መኗን በርፍልኝ ስድብና አስተያየት ተገዝሉ።በቸር እንሰንብት።








አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa