የኔት ወርኩ መበጣጠስ የማይቀር ነው
ውድ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የድርቅ
አደጋ አጋጥሟት ከችግሩ በራስዋ ጥረት ለመውጣት እየተጋች ነው።አገራችን ከማንም እገዛ ሳያሻት(እገዛ አትፈልግም ማለት አይደለም)
በዜጎቿ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመመከት ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ
ትገኛለች ሰሞኑን ከጅቡቲ በባቡራችን እንዲመጣ የተደረገው የእርዳታ እህል ለዜጎች በአግባቡ እንዲከፋፈል እየተሰራ ነው፤ለዚህ የአገራችን
ቁርጠኝነት ሊወራ ይገባል።የአገራችን ሚዲያዎችም አርቲ ቡርቲውን ጉዳይ ከማግለብለብ ይልቅ ችግሮች እንዲታረሙ ከማድረግ ጎን ለጎን
ለማንም ሳይወግኑ ይህንና የመሳሰሉትን የአገራችን ስኬቶች ቢያነሱና ለሕዝብ ቢያቀርቡ ተሰሚነት ይኖራቸዋል።
ከሰሞኑ የእንባ ጠባቂ ተቋምና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ
ኮርፖሬሽን በመተባበር ያዘጋጁት የውይይት መድረክ አንድ ነገር ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።
በአገራችን የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት መረጃን
በመሸሸግ የመገናኛ ብዙሃን ስራን አድካሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በዚህ መድረክ ላይ ተነግሮ ሰምተናል።ነገሩ እውነት ነው፤ዋናው
ነገር ይህ ለምን ሆነ? የሚለው ነው።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ከፍተኛ የመንግስት ባስልጣናትን ሰብስበው በመልካም አስተዳደርና የሙስና
ችግሮች ላይ አትኩሮ በተካሄደው ጥናት ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት አስተያየት ሲሰጡ የተናገሩት ነገር አለ፤እጠቅሳለሁ”ሁላችንም
ከዚህ ስንወጣ ኔት ወርካችን እንዳይነካ እንከላከላለን በብሄር፤በአብሮ አደግነትና በጥቅም የምንቆም ከሆነ አይሰራም፤እንዲህ መሆን
የለበትም”ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥናቱ ላይ ሽርደዳ መኖር
የለበትም ስለ መልካም አስተዳደር ችግር እስከ መቼ ነው ማውራት የምንችለው?ሲሉም ጠይቀዋል።
ሕዝቡ ስብሰባ ላይ ከሚያጋልጠኝ ስብሰብ መጥራት
የለብኝም ብሎ የተቀመጠ አመራርም እንዳለ ተጠቅሷል።
ይህ በኔት ወርክ የተሳሰረ አመራር በዚሀ አይነት
ሁኔታ መቀጠል ስለሚፈልግ አንድም መረጃ እንዲወጣ አይፈልግም፤ለይስሙላ ደፍሮ ለሚጠይቅ መገናኛ ብዙሃንም የላይ የላይዋን ነገር ደስኩሮ
ይተዋል ሌላው ተከድኖ ይብሰል ነው ነገሩ።
እንግዲህ አሁን ሁሉም ነቄ ብሏል።መንግስትም
ውርድ ከራሴ ሲል አውጇል ሕዝቡም አስፈላጊውን እገዛ ያድርግልኝ ሲል ተማፅኗል።ይህ ሊቀለበስ የማይችል የመንግስት አቋም በአሁኑ
ወቅት ሁሉም ነቅቶ እንዲጠብቅ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው ማለት ይቻላል ነገሩ የአይጥና ድመት መጠባበቅ አይነት ሆኗል።እናም ድብቁ
ትስስር የእከክልኝ ልከክልህ ግንኙነት የኔት ወርኩ መበጣጠስ የማይቀር ጉዳይ ሆኗል።
ለዚህ ማስረጃ መሆን የሚችሉ በርካታ አብነቶችን
መጠቃቀስ ይቻላል።ቀደም ሲል ሕዝብና መንግስት የሰጣቸውን ኃላፊነት ከለላ በማድረግ ለሕዝብ ሳይሆን ለራሳቸውና በአካባቢያቸው ለሚገኙ
ግለሰቦች የቆሙ የበሉ ያስበሉ በቁጥጥር ስር ውለው በሕግ ተጠያቂ ሆነዋል።ጉዳያቸው በሕግ ተይዞ በመጠየቅ ላይ የሚገኙ ወጪት ሰባሪዎችም
እንዳሉ ይታወቃል።
እነዚህ መቼም ቢሆን የኢትዮጵያ ወዳጅ ይሆናሉ
ተብሎ አይታሰብም፤የህግ ፍርዳቸውን ጨርሰው ሲወጡም ወደ ውጭ አገራት ሸሽተው ከፅንፈኛ ትምክህተኞችና ጠባብ ኃይሎች ጋር በመደባለቅ
ነጋ ጠባ የሚደሰኩሩትን እናውቃለን።
አገር ውስጥ የሚገኙ ኔት ወርከኞችም ቀናቸውን
ይጠብቃሉ እንጂ ኔት ወርካቸው በፍፁም መበጣጠሱ የማይቀር ነው።ስለዚህ በአሁኑ ወቅት አዋጭ የሚሆነው ለግል ቆሞ ከመንፈራገጥ የኢህአዴግን
መስመር በማስቀደም ራስን ነፃ ማውጣት ብቻና ብቻ ነው።
በጥቅም ተደልለው በኔት ወርክ የተሳሰሩ የኢህአዴግ
መንግስት የሚወድቅ መስሏቸው ከድርጅታዊ መስመሮች ለቀው የወጡ፤ከትምክህተኛ ጠባብና ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር የተወዳጁ ግለሰቦች በራሳቸው
ላይ ትክክለኛውን ሂስ በማቅረብ ጀግንነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
ዋ 7 ሚሊየን የኢህአዴግ አባላትና የኢትዮጵያ
ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ኃይል ቀላል መስሏችሁ የተጃጃላችሁ ካላቸሁ ተሸውዳችኋልና አስቡበት።እናንተ ራሳችሁን አጋልጣችሁ ከሰጣችሁ የኢትዮጵያ
ሕዝብ ጀግና እንደሚላችሁ አትጠራጠሩ።”ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል”የዘመናት አመለካከት ችግር ውጤት ስለሆናቸው ማንም አይፈርድባችሁም።ስለዚህ ተሽቀዳደሙና ተናዘዙ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ