ኢህአዴግ ውስጥ ስልጣን ለተልዕኮ እንጂ የብሔርና የድርጅት ተፅዕኖ ለመፍጠር አላማ አይውልም-አቶ ደመቀ መኮንን



የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ከበኩር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ብአዴን ለአማራው ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ ማንነት መከበርና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መዘርጋት ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።


የህወሓት ታጋዬችና የኢህዴን ታጋዬች በአንድ ላይ እየታገሉ በአንድ ጉድጓድ እየተቀበሩ ለድል መብቃታቸውን አቶ ደመቀ አስታውሰው፥ አደጋና መስዋትነት ሲያጋጥምም ቀድሜ እኔ ገብቼ ልሞክረው እየተባባሉ ለድል የበቁ ጠንካራ ድርጅቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ ሂደትም ሁለቱም የራሳቸው ኘሮግራሞች እና የመታገያ አጀንዳዎች የነበሯቸው እና ድርጅታዊ ነፃነታቸውንም ጠብቀው የመጡ እንደሆኑም ነው ያስታወሱት።

ከድል በኋላም ቢሆን ኢህአዴግ እንደ ግንባር የሚተዳደርበት ኘሮግራም እና ህገ ደንብ እንደቀረፀና ኢህዴን ብአዴንም ሆነ ሌሎቹ አባል ድርጅቶች ከዚያ የሚቀዱ ድርጅታዊ ኘሮግራሞች እንዳሏቸውም አቶ ደመቀ አስረድተዋል።

ኢህአዴግ ከእያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት በተውጣጡ እና እኩል የመወሰን ስልጣን ባላቸው 180 የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ተሰይሞ በጋራ የሚመራ ድርጅት እንደሆነ የገለፁት አቶ ደመቀ፥ ምክር ቤቱ ከእያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት የተመረጡ ዘጠኝ-ዘጠኝ በድምሩ 36 ስራ አስፈፃሚ አባላት እንዳሉት ነው የጠቆሙት።

ከዚህም ባሻገር የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሮችም 180 ዎቹ የምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ የሚሰየሙ መሆኑንና 36ቱም ሥራ አስፈፃሚዎች ለሀገር እንደ ኢህአዴግ በአንድ የሚሰሩ፣ ለየብሔራዊ ክልሎቻቸውም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ይበጃል የሚሉትን የሚወስኑበት ድርጅታዊ ነፃነት እንዳላቸው አብራርተዋል።

ኢህአዴግ ውስጥ ኢህዴን/ብአዴንም ሆኑ ሌሎች ድርጅቶች የህወሓት ተፅዕኖ አለባቸው የሚሉ ሰዎች አንድም የኢህአዴግን አሰራር ካለማወቅ አልያም አንድን የተለየ አካል ነጥሎ በመምታት የተለየ አላማቸውን ለማሳካት የሚያስቡ ናቸው ብለዋል።

አቶ ደመቀ ኢህአዴግ ውስጥ ስልጣን ለተልዕኮ እንጂ የብሔርና የድርጅት ተፅዕኖ ለመፍጠር አላማ እንደማይውል መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa