Waca dhiphootaa finiinsuuf
Dhiyeenya kana waa'ee ergaa sirba Haacaaluu Hundeessaa irratti barreefama tokko waanan barreesseef Namoonni tokko tokko akka malee wacanii turan.Dhugaa dubbachuuniifi barreessuun kan daran cimee itti fufu ta'u.
Iyyi Dhiphootaa fayyadamtummaa Saba Oromoo irratti kan dhufe waan ta'eef kana falmuuniifi dhugaa jiru itti himuun murteessaadha.
Dhiphoonni amantanis amanuu baattanis Sirboonni Haacaaluu lameen maalan jiraa Oromiyaa maaltu gadhiisa,Kan Nama nyaatu nukeessa jira jedhuufi kanneen biroos Sirboota jaalalaatiin ala kan jiran hundumtuu Saba Oromootiif yaadamanii kan sirbaman Namoonni isinitti fakkaatee burjaajooftan hubadhaa.Qalbii jijjiirradhaa.
Haacuuluun jedhus jechuu baatus Oromiyaa eenyumtuu gadi hin lakkisu!!!
Maalan jiraa kukkutee nanyaatee jiraa
የሃጫሉ ሁንዴሳ ዘፈን እና የዋሆች እብደት
ማለን ጂራ
በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሰሩ የኪነ ጥበብ ስራዎች የብሄሩን ቋንቋ ለማሳደግ እየተደረገ ባለው
ጥረት ውስጥ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው።እስከ አሁንም
ፍቅርን ጨምሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሕዝብ የቀረቡ የኪነ
ጥበብ ስራዎች ቋንቋው እንዲያድግና እንዲበለፅግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርካት ላይ ይገኛሉ።
ለነገሩ አፋን ኦሮሞ ሲደርስበት በነበረው የቀድሞ ስርዓቶች ጭቆና ምከንያት በስነ ፅሁፍ ሳያድግ የቆየ ቢሆንም በብሄሩ
ተወላጆች ጥረት ምክንያት የበለፀገና አሁንም የክልሉ የትምህርትና
የስራ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ነው።ወደፊት የሚደርስበትን ደረጃ ደግሞ አብረን የምናየው ይሆናል።
ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳዬ ልመልሳችሁና “ማለን ጅራ” ሲል አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በቅርቡ ለቋት የዋሆች የሚያብዱባት አንድ
ሲንግል ነጠላ ዘፈን አለች፤በሰላሌና አካባቢዋ የሕዝብን ዜማ በመጠቀም ተቀነባብራ የተሰራችው ይህች ዘፈን አሁን ሲታይ ብዙዎች ያብዱባታል።ለምን?
በማለት መጠየቅ ጠቃሚ ነው።
“ማለን ጂራ ጨጨብሴ ነኛቴ ጂራ” የለሁም እንክትክት አድርጎ በልቶኛል ማለት ነው።በፍቅር ተመስላ የተዜመችው ይች የሃጫሉ
ነጠላ ዘፈን ውስጠ ወይራ መሆኗን ብዙዎች ያውቃሉ።እያወቁ ማበድ የፈለጉ ደግሞ እያበዱባት ነው።
በኦነጋዊ አመለካከት ተጠምቃ በፊንፊኔ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ የቦታ ስሞችን በመጠቃቃስ የተዜመችው ነጠላ ዜማ ሃጫሉ ሁንዴሳ ማለን ጅራ ጨጨብሴ ነኛቴ ጅራ እያለ
ሲያቀነቅናት ሕዝብን በቁጭት የማነሳሳት አላማ እንዳላት መገንዘብ ተገቢ ነው።
የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ባካሄደው መራራ ትግል ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረውለት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሆኖ በሰላማዊ
ሁኔታ እራሱን በማስተዳደር ላይ ያለና ለአገሩ ኢትዮጵያ እድገትም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ታለቅ ሕዝብ
ነው።ታዲያ ጠባቦች ምን አድርግ እያሉት ነው ይህን ታላቅ ሕዝብ?
ጋረ ጅጉ ህንመሌ መፍረስ የሌለበት ተራራ ተናደ(የኦሮሞ ሕዝብ)
ማለን ጅረ ጨጨብሴ ነኛቴ ጂራ እንክትክት አድርጎ በልቶኛል ይህ ስርዓት አልጠቀመኝም እንክትክት አድርጎ በላኝ እንጂ
መሬቴን ቀምቶ ለባለሃብት ሰጠ እትብቴ ከተቀበረበት ተፈናቀልኩ እንደ ማለት ነው።
ጠባቦች የኦሮሞ ሕዝብ ተጠቃሚነት ቀጣይነት እንዳይኖረው የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉነው።ሃጫሉን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የኦሮሞ
ዘፋኞች ቀደም ሲልም የኦነግ ተላላኪ ሆነው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሰርተዋል።የጠባቡን ቡድን የጥበት መርዞች ረጭተዋል፤ግን ደግሞ ለጥቅምና
መብቶቹ መከበር የቆመ ኩሩና ጀግና ሕዝብ ስላለ ምንም ማድረግ አልቻሉም።በሻዕቢያ ጉያ ተሸጉጠው እየተፍጨረጨሩ ያሉትም አሁንም ወደፊትም ምንም ማድረግ አይችሉም።ባዶ ሩጫና ጫጫታ ብቻ፤እና ትርጉሙ ሳይገባችሁ በሃጫሉ
ሁንዴሳ ሲንግል በማበድ ላይ ያላችሁ ወገኖቼም ይህን ተረድታችሁ አደብ ብትገዙ አይሻልም ትላላችሁ?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ