እራስን በራስ የመተቸት ወይም የመንቀፍ ችሎታ ባለቤት-ኢህአዴግ
የኢህአዴግ
ጠንካራ ጎን የትም አይሄድም ማትኮር የሚያስፈልገው አሉታዊ ነገሮቹ ላይ ነው ለምን ቢባል ከእግዝአብሄር በታች የኢትዮጵያ መድህን
የኢህአዴግ መስመር ብቻ ነውና ይህን ማለት ለዘላለም ከኢህአዴግ መስመር
የተሻለ ሊፈጠር አይችልም ማለት አይደለም
ቀደም
ሲል በኢህአዴግ ደካማ ጎኖች ላይ በማትኮር የሚናገሩት አባላቱ ብቻ ነበሩ፤አሁን ባለው ተጨባጨ ሁኔታ ግን ስህተት ሲፈጠር ጠያቂ የሆኑትና የሚሞግቱት አባላት
ብቻ ሳይሆኑ ሕዝቦችም ጠያቂ ሆነዋል
ጠያቂ
ሕብረተሰብ መፍጠር ችያለሁ እያለ ያለው ኢህአዴግም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል በራሱ ስራ እራሱን የመተቸትና የመንቀፍ ችሎታ ባለቤት
የሆነው ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ለሩብ ክፍለ ዘመን መርቷል
በ25ቱ
አመታት ቆይታ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በራሳቸው ቀጣይ ተሳትፎና በኢህአዴግ ትክክለኛ መስመርና አመራር ብዙ ለውጦችን አይተዋል፤በማየት
ላይም ይገኛሉ
በፖለቲካ፤በኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ዘርፎች እስከ አሁን የተመዘገቡ አንፀባራቂ ድሎች በተጨባጨ ያሉ ስለመሆናቸው ዋነኞቹ ምስክሮች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና
ሕዝቦች ናቸው
ከዚህም
በተጨማሪ ተላላኪዎቻቸውን በማሰማራት(ሻዕቢያ ብቻ አይደለም) የራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት ሲሉ የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ ከሚሹ
የውጭ ኃይሎች በስተቀር አለም አቀፉ ህብረተስብ ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ እየተለወጠች ስለመሆኗ ምስክርነቱን ሰጥቷል፤እየሰጠም ነው
እዚህ ላይ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኗል ማለት የሚችል አይኖርም
እንግዲህ
በብዙዎች የተንቆለጳጰሰው ድላችን ቀጣይ መሆን እንዲችል ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወገንና ዜጋ ኃላፊነትና ግዴታ አለው ምክንያቱም
ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን አገር ናትና
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ