ግብፅ የአለማችን አራተኛዋ የጦር መሳሪያ ገዥ ሀገር መሆኗ ተጠቁሟል
አይ ኤች
ኤስ የተሰኘው የአሜሪካ ኩባንያ የ2015ቱን አለም አቀፍ የመከላከያ መሳሪያዎች ሽያጭ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
በዚህ
ሪፖርት መሰረት ግብፅ በ2015 ለጦር መሳሪያ ግዥ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አውጥታለች።
ይህም
ሀገሪቱ በ2013 ወጪ ካደረገችው የ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከእጥፍ በላይ ብልጫ ያሳየ ነው።
የሪፖርቱ
ፀሃፊ እና በአይ ኤች ኤስ ከፍተኛ የመከላከያ ጉዳዮች ተንታኝ ቤን ሞርስ እንደገለጹት፥ ከፍተኛ ወጪ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያ
ግዢዎች በግብፅ ወዳጆች ፈረንሳይ እና የባህረ ሰላጤው አርብ ሀገራት የተሸፈኑ ናቸው።
ግብፅ
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በ2011 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ኢኮኖሚዋ ፈተና ገጥሞታል።
ባለፈው
የግንቦት ወር መጨረሻም የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 17 ነጥብ 52 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ነበር።
ይህም
ከ2011 በፊት ከነበረው 36 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከግማሽ በታች የወረደ ነው።
ፕሬዚዳንት
አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ግብፅ ከፈረንሳይ እና አሜሪካ የጦር መሳሪያ ግዢዎችን ፈፅማለች።
ሀገሪቱ
ራፍል ተዋጊ ጀቶች እና የጦር መርከቦችን ከፈረንሳይ፤ ኤፍ 16 ተዋጊ ጀቶች እና ታንኮችን ደግሞ ከአሜሪካ መግዛቷንም ሪፖርቱ ያሳያል።
ግብፅ
የጦር መሳሪያ ግዢ እና የደህንነት ጉዳይ ፖሊሲዎቿን ለማጠናከርም ከሩስያ እና ጀርመን ጋር የጦር መሳሪያ ግዢ ስምምነቶችን ፈፅማለች።
ሳኡዲ
አረቢያ፣ ህንድ፣ አውስትራሊያ፣ ግብፅ እና ደቡብ ኮሪያ የአለማችን ቀዳሚ 5 የጦር መሳሪያ ገዢ ሀገራት ናቸው ብሏል ሪፖርቱ።
ኢራቅ
ከግብፅ የሚስተካከል ወጪ ብታወጣም ከመሳሪያ ግዚዎች ይልቅ ለወታደራዊ ዘመቻዎች፣ ለሰው ሀብት ስራዎች እና ለቁሳቁስ ግዥዎች በስፋት
አውላዋለች የሚለውም በሪፖርቱ ተነስቷል።
አመታዊው
ሪፖርት የሳኡዲ አረቢያ የጦር መሳሪያ ግዢ በፍጥነት መመንደጉንና ሀገሪቱ አለም አቀፉ የጦር መሳሪያ ሽያጩ ባለፈው አመት ከ10
በመቶ በላይ እንዲያድግ ማድረጓን ነው ያመለከተው።
ለሪያድ
የጦር መሳሪያ ግዢ ጭማሪ በየመን እና ኢራን ፖለቲካ ውስጥ ያላት ተሳትፎ በምክንያትነት ተቀምጧል።
ሀገሪቱ
ባለፉት አመታት ዩሮፋይተር ታይፎን ጀቶችን፣ ኤፍ 15 የጦር አውሮፕላኖችን እና አፓች ሄሊኮፕተሮችን፣ አነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላኖች
(ድሮኖችን) እና የስለላ መሳሪያዎችን ገዝታለች።
አለም
አቀፉ የጦር መሳሪያ ገበያ በ2015 65 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የደረሰ ሲሆን፥ ከ2014ቱ የ6 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እድገት
አሳይቷል።
ይህም
ካለፉት አስርት አመታት ትልቁ አመታዊ እድገት መሆኑን ነው አይ ኤች ኤስ የጠቆመው።
ተቀማጭነቱን
ኮሎራዶ ያደረገው ኩባንያው አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ገበያው ምን እንደሚመስል በ65 ሀገራት ላይ የተደረጉ ጥናቶች ላይ ዳሰሳ
አድርጓል።
ምንጭ፦
ሲሲቲቪ አፍሪካ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ