ኢትዮጵያ እጩ ሆና የቀረበችበት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ምርጫ ዛሬ ይካሄዳል
ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ እጩ
ሆና የቀረበችበት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ምርጫ ዛሬ በኒውዮርክ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት
ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የምታገለግል ከሆነ በአለም አቀፋዊ ትብብርና በጋራ
ሰላምና ደህንነት ላይ ያላትን የጸና አቃም አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ኢትዮጵያ በቀድሞው ሊግ ኦፍ
ኔሽንስ በአሁኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች አባልነቷ ለአለም ዓቀፍ ትብብር መጎልበትና ለጋራ ደህንነት መርሆዎች መከበር
ጉልህ ሚና እየተወጣች ዘልቃለች።
ከ1950ዎቹ አንስቶ እየጎላ
በመጣው አካባቢያዊና ዓለማቀፍ የሰላምና ፀጥታ የማረጋገጥ ሚናዋ ከኮሪያ እስከ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲና ላይቤሪያ አሁን ደግሞ በሶማሊያ፣
አብዬ ዳርፉርና ደቡብ ሱዳን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገች ነው።
በአሁኑ ወቅት ለተባበሩት መንንግስታት
ድርጅት ትልቅ ቁጥር ያለው ሰላም አስከባሪ ጦር በማዋጣት በዓለም 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የስደተኛ
ቁጥር በማስተናገድም ኢትዮጵያ ያላት ሚና ከፍተኛ ነው።
በታሪኳ ለ3ኛ ጊዜ በቀጣይ የጸጥታው
ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ከተመረጠችም እነዚህን ሚናዎቿንና የአፍሪካን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የምታደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክራ
እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ገልፀዋል።
አገሪቱ ለመመረጥ የሚያስችላትን
ቅስቀሳ ለወራት ስታደርግም ቆይታለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት አምስት ድምጽን በድምፅ የመሻር ስልጣን ያላቸው አባላትና በየሁለት አመቱ ከየቀጠናው የሚመረጡ 10 አባል
አገራት በድምሩ 15 አባል አገራት የሚካተቱበት መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ