ለውርስ ስትል ልጇን ያስገደለችው እናት በጽኑ እስራት ተቀጣች
ለውርስ
ስትል ልጇን ያስገደለችው እናት ከእነ ተባባሪዎቿ በጽኑ እስራት ተቀጣች።
ተከሳሾች
1ኛ ሳጅን ሃብታሙ አስፋው፣ 2ኛ ዘይን አወል ሁሴን፣ 3ኛ መሃመድ አሊ፣ 4ኛ መሃመድ የሱፍ አሊ እና 5ኛ አቤል ፋንታሁን ይባላሉ።
3ኛ ተከሳሸ
የከሚሴ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ሌሎቹ ተከሳሾች የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።
የሰሜን
ሸዋ ዞን ፍትሀ ቢሮ የአቃቢ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው፥ 2ኛ ተከሳሽ የሟች ታጁ መሃመድ እናት ስትሆን፥ ከሟች አባት ጋር የነበራትን
ትዳር በመፍታትና ንብረት በመካፈል ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ፍቅር ትጀምራለች።
ተከሳሿ
ሟች ልጇን ቤቱ ተሸጦ እንካፈል በማለት ትጠይቀው እንደነበርም አቃቢ ህግ በክሱ አመልክቷል።
ነሃሴ
24 ቀን 2007 ዓ.ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን፥ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉ ተከሳሾች ሟች የእንጨት ስራ በሚሰራበትና በሚያድርበት ሙሳ
ይመር የቤትና የቢሮ የእንጨት ስራ ድርጅት በማቅናት ከተኛበት ቀስቅሰው በመውሰድ ትልቁ መስጊድ እየተባለ በሚጠራው መታጠፊያ ስፍራ
ላይ ግራ ደረቱን በተደጋጋሚ በሽጉጥ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጋቸውን የአቃቢ ህግ ክስ ያስረዳል።
በማግስቱም
አስከሬኑን 5ኛ ተከሳሽ በባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ (ባጃጅ) ጭኖ ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾቸ ጋር በይምሎ ቀበሌ አራዳ በር እየተባለ
በሚጠራው ስፍራ ጥለው ተሰውረዋል።
ይሁን
እንጂ ድርጊቱን የተከታተሉ 2 የአይን እማኞች ባደረጉት ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው በግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ተከሳሾቹ
ክሱን ክደው የተከራከሩ ቢሆንም፥ አቃቢ ህግ የሰነድ እና የ2ኛ ተከሳሽ ሴት ልጅ (የሟች እህት) እና ሁለት የአይን እማኞችን ምስክር
አድርጎ በማቅረብ ክሱን ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል።
የሰሜን
ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎትም፥ ተከሳሾቹን ጥፋተኛ በማለት በእርከን 38 መሰረት የቅጣት ውሳኔውን አሳልፏል።
በዚህም
1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣ 3ኛ ተከሳሽን በ25 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም 5ኛ ተከሳሽን 2 አመት
ከ9 ወራት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።
Source:FBC
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ