አላርፍ ያለች ጣት……
አንዳንድ የአገራችን የግል ነፃ
ፕሬሶች ኢህአዴግን ካልሰደቡና ካላበሻቀጡ የሚፅፉት ሁሉ የማይሸጥላቸው መሰለ፤ አሁን ታትመው በመውጣት ላይ ከሚገኙት የግል ነፃ
ፕሬሶች ውስጥ የሚጠቀሰው “አዲስ ገጽ” የተባለ መፅሄት በዚህ ሳምንት
እትሙ በግንቦት 20 ላይ አትኩሮ ለአባብያን ያደረሳቸውን የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ፅሑፎች ለማንበብ ከሰሞኑ እድሉን አግኝቼ ነበር
ኤሊያስ ገበሩ የተባለ ዚህ መፅሄት
ዋና አዘጋጅ “የግንቦት 20 የክፋት ፍሬዎች” በሚል ርዕሰ የጻፈውን
በጥቂቱ ልጥቀስ ኤሊያስ “የዜጎችን የተለየ ሃሳብ ለማፈን ሲባል ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ
አንዱ የክፋት ልቦና የወለደው የግንቦት 20 ፍሬ ነው፤ተሸበርኩ ብሎ
የሚያሸብር ዜጎችን በፍርሃት ውስጥ የሚጥል የሚያሸማቅቅ፤ዜጎች በአገራቸው ሁለተኛ ዜግነት እንዲሰማቸው የሚያደርግና መንግስታዊ ሽበርተኝነት
አዋጅ ነው”ይለናል ነው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው
እውነት ነው የፀረ ሽብርተኝነት
ህጉ ለኤሊያስና የእርሱን አይነት አስተሳሰብ ላላቸው ጥቂት ሰዎች አይመችም ለእኔ ህጉ አልተመቸኝምና ለእናንተም አይመችም ማለት
ግን ጊዜው ያለፈበት የእኔ አውቅልሃለሁ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው
በአገራችን የፀረ ሽብርተኝነት
ህግ በመኖሩ 90 ሚሊየን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም ወጥቶ እየገባ ነው፤በሌሎች አገራት ዘወትር የምንመለከተው አሰቃቂ የሽብር አደጋ
የለም፤ በአሸባሪዎች እኩይ ድርጊት ምክንያት የኢትዮጵያ የልማትና የዕድገት ግስጋሴ አልተደናቀፈም
የድርቅ አደጋና አንዳንድ እጅግ
በጣም ጥቃቅን ችግሮች ቢያገጥሙም የኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ አልተደናቀፈም ኤሊያስ ገብሩና ጥቂት መሰሎቹ ግን በፅናት የሚፈልጉት በአሸባሪዎች
የቦምብ ፍንዳታ ደም ሲፈስ ማየት፤ክቡሩ የሰው ልጅ ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር፤ንብረት እንዲወድም፤የአለም ህብረተሰብ ለኢትዮጰያ ከንፈሩን
እንዲመጥና በመጨረሻም ኢህአዴግ ከስልጣን ወርዶ አለቆቻቸው ከስልጣን መንበሩ ጉብ እንዲሉ ነው በቃ! ከዚህ ያለፈ አይደለም
ለራሳቸው እንጂ ለሌሎች መብት
መከበር ደንታ እንደሌላቸው በተግባራቸው በማረጋገጥ ላይ የሚገኙት “አዲስ ገጽ”ን ጨምሮ የአንዳንድ የግል ነፃ ፕሬስ ሰዎች ድንፋታ
ግን ሁሌም ይገርመኛል ለማንኛውም አላርፍ ያለች ጣት አንድ ቀን መቆረጧ አይቀርም ይላል ያገሬ ሰው
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ