አዲሱ ትውልድ ለቀጣዩ ኃላፊነት ራሱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል-አቶ ሙክታር ከድር

አዲሱ ትውልድ ለቀጣዩ ኃላፊነት ራሱን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅበት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙታር ከድር አሳስበዋል

የግንቦት 20 25ኛ ዓመት የብር እዮቤልዩ በዓል ትናንት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች በአዳማ አባ ገዳ አዳራሽ ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት ተከብሮ ውሏል


በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር ባስተላለፉት ጠንከር ያለ መልዕክት ወጣቱ ትውልድ የስርዓቱን አደጋዎች ጠባብነት፤ትምክህተኝነት፤አክራሪነትና ኪራይ ሰብሳቢነትን በመከላከል ለቀጣዩ ኃላፊነት ራሱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል ብለዋል

የክልሉ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ቀጣይ መሆን የሚችለው በእነዚህ የስርአቱ አደጋዎች ላይ ያለምንም ማቅማማት በቁርጠንነት ቀጣይ ትግል ሲደረግ ብቻ እንደሆነ በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ግንዛቤ ሊያዝ እንደሚገባና የተለዩት የስርአቱ አደጋዎች በቸለተኝነት የሚታለፉ ከሆነ የሚደርሰው ጥፋት ክልሉንና አገሪቷን ወደ ኋላ የሚመልስ እንደሆነ ተናግረዋል

በፓናል ውይይቱ ላይ ባለፉት 25 አመታት በኦሮሚያ ክልል በፖለቲካ፤በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ወይይት እንደተካሄደ ታውቋል


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa