መዋሸት ካልቀረ እንደ አምባሳደር በየነ ርዕሶም

በአገራችን በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች የመንግስት ስራዎችን በተመለከተ የሃሰት ሪፖርት ያቀርባሉ በሚል ሲወቀሱ ቀደም ሲል ሲሰማ ቆይቷል


እነዚህ የሃሰት ሪፖርት አቅራቢዎች ህብረተሰቡ በየዘርፉ በቂ አገልግሎት ሳያገኝ እንደቆየ አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ጉዳይ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ እረ ምንም ችግር የለም ሁሉም ነገር በሰላማዊ ሁኔታ እየሄደ ነው ብለው የውሸት ሪፖርቶችን ለበላዮቻቸው ሲልኩ መቆየታቸው ተረጋግጧል

የሃሰት ሪፖርት አቅራቢዎቹ የቆዩበት ሁኔታ በአካባቢያቸው ህብረተሰብ በደንብ ይታወቃልና በእኩይ ድርጊታቸው ተጋልጠው ቀኑ ሲደርስ እንቢ ለመብቴ ብሎ ለእንግልት ተዳርጎ የቆየው ሕዝብ  ሆ ብሎ ሲነሳ የሚገቡበትን አጥተው ለበላዮቻቸው እረ ልናልቅ ነው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ይላክልን ሲሉ ልመና ውስጥ መግባታቸውም ትዝብት ውስጥ ጥሏቸው አልፏል

የሃስት ሪፖርት አቅራቢዎቹ በኪራይ ሰብሳቢነት በሽታ ተተብትበው የቆዩ መሆናቸው ተግባራቸው ፍንትው አድርጎ አጋልጧልና ቀስ በቀስ ይኸው ጥጋቸውን እንዲይዙ እየተደረገ ነው አሁንም ገና ነው፤ያልተደረሰባቸውና ጊዜው ሲደርስ ዋጋቸውን ማግኘት ያለባቸው እንዳሉ ይታመናል

እንደ አገራችን ገልቱ የስራ ኃላፊዎች ሁሉ በጎረቤት አገር ኤርትራም የሃሰት ሪፖርትን የማቅረብ ተመሳሳይ ችግር ስለመኖሩ ከሰሞኑ በይፋ ተጋልጧል

ነገሩ እንዲህ ነው፤ሰውዬው በኬንያ የኤርትራ አመባሳደር ናቸው በየነ ርዕሶም ይባላሉ በአንድ የኬንያ ቴሌቪዥን ላይ  በኬንያ የኢትዮጵያ አመባሳደር ከሆኑት ዲና ሙፍቲ ጋር ለቃለ መጠይቅ ቀረቡ፤ብዙ ነገርም ደሰኮሩ ኢትዮጵያንም በአናሳው ብሄር ህወሃት የትግራይ ተወላጆች እየተገዛች ያለች አገር ሲሉ አጣጣሉ፤የባጥ የቆጡን እያነሱም ቀባጠሩ ቀደም ሲል ኤርትራ የመንን እንድትወር ድጋፍ ያደረገችው ኢትዮጵያ ናት ብለው ሲናገሩም ተሰማ

አምባሳደር በየነ ርዕሶምን የበለጠ ውሸታምና ቀላል የሱሙኒ ጌሾ ያደረጋቸውን ነገርም ከአንደበታቸው ሰማን የኤርትራ ስደተኞች ቁጥር 8 መቶ ብቻ ነው አሉ ክቡር አምባሳደር በየነ

አምባሳደሩ  በአዲስ አበባና አካባቢዋ ያሉ የኤርትራ ስደተኞች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ  መሆኑ እየታወቀ አፍጥጦ ያለውን ሃቅ በመደበቅ የሃሰት ሪፖርት ለማቅረብ ያስገደዳቸው ምንድነው?

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa