የሕዝባዊ ወገንተኝነት ውሳኔዎች
ጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅና ሹመት አፀደቀ
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ አቶ ለማ መገርሳ በጉባኤው ላይ
ባሰሙት ንግግር መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል
የጨፌ ኦሮሚያ አባላት በክልሉ መልካም አሰተዳደርን በማረጋገጥ
ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በቅርበት ተከታትለው አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ለማ አሳስበዋል
የጨፌ ኦሮሚያ 1ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስተቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ለግማሽ ቀን ባደረገው ቆይታ በተጨማሪ የበጀት ጥያቄ
ላይ ተወያይቶ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፅድቋል
ከ1 ቢሊየን 652 ሚሊየን ብር በላይ የተጨማሪ በጀት ጥያቄ የቀረበው የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን
ለማጠናቀቅ፤በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋምና በህዝብ ተሳትፎ ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የቀሩ የልማት
ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንደሆነ ተገልጧል
አስቸኳይ ጉባኤው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና
ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመትም አፅድቋል
በዚሁ መሰረት አቶ አዲሱ ቀበኔሳ ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን ዑስማን ደግሞ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ምክትል ፐሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን የጨፌ ኦሮሚያ ፅህፈት ቤት ምክትል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃለፊ አቶ ሃብታሙ ደምሴ ተናግረዋል
ቀደም ሲል የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደሞዜ ማሜ ምክትሉ ደግሞ አቶ ቦጃ ታደሰ ሆነው ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይታወቃል
በሌላ በኩል አስቸኳይ የጨፌ ስብሰባ የሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ያለ መከሰስ መብትን ለማንሳት
በኦሮሚያ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የቀረበውን ጥያቄ አጽድቋል፡፡
በምክትል ፕሬዚደንት ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ የነበሩ የአቶ ዘላለም ጀማነ ያለ
መከሰስ መብት አንስቷል፡፡
አቶ ዘላለም ከፍተኛ የክልሉ መንግስትና ድርጅት አመራር በነበሩበት ወቅት የተጣለባቸውን
ሕዝባዊ አደራና ወገንተኝነት ወደ ጎን በመተው ፤በተሰጣቸው ኃላፊነት በመጠቀም የማይገባቸውን ከፍተኛ ኃብት በማካበትና የሕዝብና
የመንግስት ኃብትና ንብረትን በመዝረፍ በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥረው በቂ መረጃ እንዳለው የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን
በመጠቆሙ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡
እንዲሁም የሱሉልታ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩና በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ጨፌ
ተወካይ የነበሩት አቶ ዲሮ ደሜ ፤በመንግስት ሥልጣን ያለአግባብ በመጠቀም በስማቸውና በዘመዶቻቸው ሥም በርካታ የሕዝብና የመንግስት
መሬትና ንብረት መዝረፍ ወንጀል ስለተጠረጠሩ በፀረ-ሙስና ኮሚሽኑ ጥያቄ መሰረት ጨፌው ያለ መከሰስ መብታቸውን አንስቷል፡፡
የጨፌው አባላትም በጉዳዩ
ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኃላ ውሳኔው ትክክለኛና ሕዝባዊ ወገኝተኝነትን ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ