"ድመት መልኩሳ አመሏን አትረሳ" ሆኗል ነገሩ
"ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል"እንዲሉ ሕወሃት ለአመሉ ለአራተኛ ዙር ወረራ እየተዘጋጀ ነው ማለት ተገቢ ይሆናል
እንደ ዜጋ ለአገርህ አሳሳቢ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ መናገር፤ መፃፍ፤መከራከር መኮነን ያለበት አይመስለኝም አንዳንዶች ይህን ድፍረቴን እንደማይወዱት አውቃለሁ፤አልፈርድባቸውም ግን ዝም ማለት አልችልም!
እኔ የምለው በትግራይ ሕጋዊ የሚባል መንግስት አለ እንዴ? የትግራይ መንግስት የማለት ድፍረትስ ከየት መጣ?የሰላም ስምምነቱ በትግራይ ሕጋዊ መንግስት እንደሌለ፤ሕወሃት በተገደበ ጊዜ ውስጥ ታጣቂዎቹን ትጥቅ እንዲያስፈታ፤ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብ ያዛል
የኢትዮጵያ መንግስት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች ሰብአዊ ድጋፎችን በማቅረብ ላይ መሆኑን፤መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶች በመላው ትግራይ እንዲጀመሩ ያልተቋረጠ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል
እስኪ እንጠይቅ! የሕወሃት ቁንጮዎች በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ከሰላም ስምምነቱ ጉዳዮች ውስጥ የትኛውን ፈፅመው በተግባር አሳይተዋል?የሚጠበቅባቸውን ስራ በወቅቱ መፈፀም ትተው በፌዴራል መንግስት ላይ ቅሬታ የማሰማት ድፍረትስ ከየት ተገኘ?"ድመት መልኩሳ አመሏን አትረሳ" ሆኗል ነገሩ
የአደራዳሪዎቹና ታዛቢዎቹ ድምፅስ ምነው ጠፋ? ስምምነቱን በማይተገብር አካል ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለው የተናገሩ መሰለኝ፤ምነው ታዲያ የሕወሃት ሰዎች እንደለመዱት ያሻቸውን ሲያደርጉና ሲናገሩ ዝም ጭጭ አሉ?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ