የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት አበረታች ደረጃ ላይ መሆን




(Muddee 18,2015 Finfinnee) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ ማቅናት የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት አበረታች ደረጃ ላይ መሆኑንና መንግስት ለሰላም ቁርጠኛ አቋም መያዙን ያመላክታል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ገለጹ፡፡

 ኡስታዝ ካሚል  እንደተናገሩት፣ ከሁለት ዓመታት በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በአቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የልዑካን ቡድን ወደ መቀሌ መሄዱ ልዩ ደስታን ፈጥሮላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ማቅናት ሰላምን ከማብሰር በዘለለ በወረቀት ላይ የሰፈረው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነቱ ወደ መሬት መውረዱን፣ ለትግራይ ሕዝብ የሚደረገው ሰብዓዊ እርዳታ ከሪፖርት ባሻገር በተጨባጭ ምን እንደሚመስል እና የመሰረተ ልማቶችን ግንባታ መገምገም እንደሚጨምር የገለጹት ኡስታዝ ካሚል፤  በተጨማሪ የሕዝቡን ፍላጎት ለማወቅ እና ጥያቄውን ለማዳመጥ እድል እንደሚፈጥርም አመልክተዋል፡፡

ልኡካን ቡድኑ የሰላም ስምምነቱ ወረቀት ላይ በሰፈረው መሰረት በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ያለው እንቅስቃሴ የማየትና የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለማወቅና ለማስተካከል እንደሚረዳ ጠቁመዋል፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረው አለመግባባት በስምምነት እልባት ማግኘቱ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ኃይል በንግግር ካልሆነ በቀር በጦርነት ማሸነፍ እንደማይችል እንዲሁም ሌሎችም ወደ ሰላም እንዲመጡ መንገድ ያሳየ ክስተት ነው ያሉት ኡስታዝ ካሚል፤ በደቡብ አፍሪካ የተደረገው የሰላም ስምምነት በር ከፋችና መላውን ሰላም ወዳድ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስደሰተ እንደመሆኑ የአሁኑ የልዑካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ጉዞ ለመላ ኢትዮጵያውያንና ለውጭ ኃይሎች ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በተለያዩ አገራት የሰላም ስምምነት ተደርጎ ግማሹ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ተግባራዊ የተደረገ፣ ግማሹ ደግሞ ያልተሳካበት ሁኔታ በመኖሩ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ አለበት ያሉት አቶ ኡስታዝ፤ ከዚህ አንጻር ግለሰቦችና ሚዲያዎች የነበረውን ቁስል ከሚያስታውሱና ጠላትነትን ከሚያባብሱ ነገሮች መቆጠብ አለባቸው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ መንግሥትም መልሶ በመገንባትና ሰብዓዊ ድጋፎችን በሚያደርስበት ጊዜ ለአማራና ለአፋር ክልሎችም ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ኡስታዝ፤ ድጋፉን በአፋጣኝ እውን ለማድረግ ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ለማግኘት ከሚደረገው እንቅስቃሴ በተጓዳኝ ክልሎችን በማስተባበር ያሉንን የውስጥ አቅሞች ለመጠቀም መጣር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

እንደ ኡስታዝ ካሚል ማብራሪያ፤ አንዳንድ የዓለም መንግሥታት ርዳታ ለመስጠት የሚያስቀምጡት ቅደመ ሁኔታ ተገቢ አይደለም፡፡ አሁን ላይ ከሁሉም የሚቀድመው ለተራበው ምግብ፣ ለተጠማው ውሃ፣ ለታመመው መድኃኒት፣ ጨለማ ውስጥ ላለው ደግሞ ብርሃን ማቅረብ ነው፡፡ ቅድመ ሁኔታዎች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚመጡ ናቸው፡፡ አሁን የተጀመረው ግንኙነት ወደ ሕዝብ ወርዶ የነበረውን ወንድማዊ ፍቅርም ወደ ቦታው መመለስ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

Maddi:የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman