ጊዜው የብልፅግና ነው!

 


አሁን ጊዜው የብልፅግና ነው!

ጊዜው የማንም አይደለም! ጊዜው የብልፅግና ነው!አምፑሏን እንደመረጥን ለምን እንዘነጋለን?ብልፅግና ፓርቲ በተሰጠው የአምስት ዓመት ጊዜው ውስጥ ያቀደውን፤ለህዝብ ቃል የገባውን ተረጋግቶ እንዳይሰራ ረባሾች ከዚህም ከዚያም እየረበሹ ነው፤የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው ግን ደግሞ ማሸነፍ አይችሉም
ይህ የረባሾች እንቅስቃሴ ምክንያቱ ብዙ ነው ዋነኛው ምክንያት ክስረታቸው ነው የከሰረ ተስፋ የለውም ተስፋ ቢስ ነው
ራሱ ተስፋ ቢስ ስለሆነ ሌላውም ተስፋ እንዲያጣ ሌት ተቀን ይጥራል፤እየሆነ ያለውም ይኸው ነው
አሁን እኛ ስለ ስለ ትምህርት ቤት መዝሙርና ስለ ሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ የምንጨቃጨቅበት ወቅት ላይ አይደለንም! ስለ ኑሮአችን ስለ ልማታችን ከአሸማቀቀን ድህነት ለመውጣት አስበን ተጨንቀን መስራት ሲገባን የማንም ውርጋጥ የከሰረ ፖለቲከኛ የሚፈጥርልንን አጀንዳ ስናራግብ እንውላለን
ይህ መሆን የለበትም ተማሪዎች ይማሩ! ስለ ውጤታማነታቸው ያስቡ ነጋዴው ይነግድ!፤አርሶ አደሩ ይረስ! ሰራተኛው ይስራ መምህሩ ያስተምር!ሌለላውም የህብረተሰብ ክፍል በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን ይንቀሰቀስ!
ይህ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ የተሻለ የዕድገትና የብልፅግና ሃሳቦችን ማመንጨት ይችላል
ካልሆነማ ሁሉም ምንም ይሆናል ባዶ!የብልፅግና ፓርቲ ባቀደው መሰረት መስራት አይችልም፤ለውጥ ሊመጣ አይችልም እንዲሁ ስንቆራቆስ እንኖራታለን፤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶችም ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ይህ እንዲሆን የሚፈልጉ እጅግ በጣም ጥቂት ቅጥረኞች ቢኖሩም አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ጉስቁልና ኑሮ መግባት አይፈልግም
ስለዚህ የከሰሩ ኃይሎችን እረፉ!በማለት ለጋራ ዕድገትና ብልፅግና መስራት ይገባል! ያስፈልጋል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Eessa turre,Maalirra Geenyeerra? Kutaa 4ffaa