ጽንፈኝነት አገር ያፈርሳል!



ጽንፈኛ የእኔ ይበልጣል ብሎ የያዘውን አመለካከት ከግብ ለማድረስ ጉልበትን ይጠቀማል፤እውነተኛ እኔ ብቻ ነኝ፤ጽንፈኝነት ከእኔ ውጭ ያለው አመለካከት ሁሉ እውነት አይደለም በሚል ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ነው
ጽንፈኞች ከሌላው ጋር በጋራ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ጉልበትን በመጠቀም ጥቃት መፈፀምን እንደ አንድ ስልት ይጠቀማሉ፤ስለዚህ የጽንፈኞች ጉዞ መጨረሻው ጥፋት ነው
ጽንፈኞች ግለኛ ስለሆኑ መቃወም እንጂ በምክንያት መርታትን የማይችሉ፤ለማጥፋትና ለመግደል ቅድሚያ የሚሰጡ እንዲሁም በጎሰኝነት አመለካከትና የግል ጥቅምን ብቻ ማዕከል በማድረግ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ቡድኖች ናቸው፤ለፖለቲካ ትርፋቸው እንጂ ለአገር አንድነትና ለሕዝቦች የጋራ ኑሮ ግድ የላቸውም
የጽንፈኞች ድርጊት የአገርን መፍረስ ያመጣል፤ግጭትን በማስፋፋት ዜጎች እንዲተላለቁ ያደርጋል ለጽንፈኝነት በሽታ የተጋለጡ በርካታ አገራት ለአስከፊ ጉዳት ተጋልጠዋል
ይህ ካንሰር በተለያዩ አገራት ለብዙ ሰዎች እልቂት፤ለፀጥታ መደፍረስና ለተለያዩ አገራት መፍረስ መሰረታዊ ምክንያት መሆን የቻለ ነው
ጽንፈኞች በሌላ ሰው እጅ እሳት መያዝ የሚፈልጉ፤ድብቅ ተልዕኮአቸውን ከግብ ለማድረስ እንዲመቻቸው በብሄርና በእምነት ስር መደበቅን እንደ መመሪያ የሚጠቀሙ ሲሆን ይህ ድርጊታቸው ግን ለየትኛውም ወገን ከጉዳት በስተቀር ጥቅምን አያስገኝም
የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተረጋግጦ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድነት ተጠናክሮ የጋራ ብልፅግና ከግቡ መድረስ የሚችለው ሁሉም ዜጋ በጽንፈኝነት አመለካከትና ድርጊት ላይ በአንድነት መታገል ከቻለ ብቻ ነው
ሁሉም ችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙት በአንድነትና ወንድማማኝነታችን ስር ስለሆነ ጽንፈኝነትን በማራመድ አብሮነታችንን ለማፍረስና የአገርን የዕድገት ጉዞ ለማደናቀፍ በመፍጨረጨር ላይ የሚገኙ ጽነፈኞች በመመከት ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት እንዲኖር ሚናችንን መወጣት ይጠበቅብናል



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman