የሕፃናቱ ገዳይ በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ

 


ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባት ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ተወሰነ።
የቅጣት ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ በጥቅምት 15 ቀንፐ 2015 ዓ/ም የወንጀል ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።
ተከሳሿ ክሱ ከደረሳት በኋላ ጠበቃ የማቆም አቅም እንደሌላት መግለጿን ተከትሎ በፍርድ ቤቱ በመንግስት ተከላካይ ጠበቃ የህግ ድጋፍ ተደርጎላታል።
ክሱ በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ ተከሳሿ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ስትል የሰጠችውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ በጥቅምት 30 ቀን በነበረ ቀጠሮ ዓቃቢህግ የሟች ግዮናዊት እና ክርስቲና መላኩ ወላጆችን ጨምሮ ስድስት ምስክሮችን አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን አሰምቷል።
የምስክር ቃል የመረመረው ችሎት በህዳር 13 ቀን በነበረ ቀጠሮ ተከሳሿ በተሰሰችበት ወንጀል እንድትከላከል ብይን ሰየሰጠ ቢሆንም ተከሳሿ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ገልጻለች።
ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ በፖሊስ ጣቢያ የሰጠችውን የዕምነት ቃል በመያዝና የዓቃቢህግ የሰው ምስክሮችን ቃል መርምሮ በተከሰሰችበት ተደራራቢ ወንጀል የጥፋተኛ ፍርድ አስተላልፎባታል።
ከቀጠሮ በፊት የዓቃቢህግ የቅጣት ማክበጃ አስተያየት እና ተከሳሽ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ካላት በጽ/ቤት እንዲያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን።
በዓቃቢህግ በኩል ወንጀሉ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በሁለት ህጻናት ላይ የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ በወንጀለኛ መቅጪያ ስነስርዓት ህግ በአንቀጽ 39 መሰረት ተከሳሿ በሞት እንድትቀጣለት ጠይቋል።
በተከሳሿ በኩል የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌላት እና አቅመ ደካማ እናቷን እንዲሁም አራት እህቶቿን እንደምትረዳ በመግለጽ በተጨማሪም ወንጀሉን ፈጽሜ እጄን ለህግ አካል የሰጠሁና ከዕውቀት ማነስ ወንጀሉን የፈጸምኩ በመሆኑ የቅጣት ማቅለያ አስተያየቴ ይያዝልኝ ስትል አስተያየት አቅርባለች።
ያቀረበችው የቅጣት አስተያየት በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ አልተያዘም።
በእንቅልፍ ላይ የነበሩ እራሳቸውን የማይከላከሉ ህጻናትን ህይወት ያጠፋች መሆኗና የሟች ህጻናት ወላጆችን ማስረጃ ቀዳዳ የጣለች መሆኗ መረጋገጡን ችሎቱ ገልጿል።
በዚህም መነሻ ፍርድ ቤቱ ተከሳሿ ጥፋተኛ በተባለችበት ወንጀል ድርጊት በሞት እንድትቀጣ ወስኗል።
ይህ መዝገብ አንድ ወር ከ15 ቀን ውስጥ ምስክር ተሰምቶ ማስረጃ ተመርምሮ ፈጣን ዕልባት የተሰጠበት የግድያ ወንጀል መዝገብ ነው።
የሟች ህጻናት ወላጆች በውሳኔው ደስታቸውን በችሎት ሲገልጹ ተስተውሏል።

ምንጭ:የታሪክ አዱኛ ፌስ ቡክ ገፅ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman