ከ23 በላይ የመሬት ደላላዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል

 



(ሕዳር 27፣ 2015 ዓ.ም) በአዲስ አበባ እና በክልሎች ከአመራሮች ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ መሬት በህገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች እንዲሰጥ አድርገዋል የተባሉ ከ23 በላይ የመሬት ደላላዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል

በአዲስ አበባ እና በክልሎች ከተለያዩ አመራሮች፣ ባለሙያዎች ጋር በመመሳጠር አንዲሁም ለባለስልጣን ሽፋን በመሆን ከፍተኛ መሬት በህገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች እንዲሰጥ አድረገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከ23 በላይ ህገ ወጥ የመሬት ደላላዎች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ሁለተኛ የወንጀል ችሎት ነው በዛሬው ዕለት የቀረቡት።

ተጠርጣሪዎቹ በክልሎችና አዲስ አበባ ከሚገኙ በተለያየ ደረጃ ያሉ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ካርታ በህገ ወጥ መንገድ በማስወጣት ለግለሰቦች እንዲተላለፍ ማድረጋቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ በተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቂያው አቅርቧል።

በተለይም ከአርሶ አደር ኮሚቴዎች ጋር በመገናኝትና ሀሰተኛ ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማድረግ ብዙ ሺህ ካሬ ሜትር ከመሬት ባንክ ውስጥ ወጥቶ ለግለሰቦች እንዲደርስ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የይገባኛል ጥያቄ ተነሰቶባቸው በክርክር ላይ የሚገኙ ቦታዎችን በማጠር ባላቸው ግንኙነት ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጭምር መጠርጠራቸውም ተገልጿል።

የተገኘውንም መሬት ለራሳቸው የወሰዱ በመሆኑ እና ለስራ ሃላፊዎች ሽፋን በመስጠት እንዲወስዱ በማድረግ በህገ ወጥ ድርጊታቸው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ከፍተኛ ሃብት ያካበቱ በመሆኑ በህገ ወጥ የድለላ ስራ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው በምርመራ ከህዳር 23 እስከ 25 ቀን 2015ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው፡፡

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮም የምስክሮችን ቃል በመቀበል፣ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ሰነዶችን በማሰባሰብ እና ከተለያዩ ባንኮች የሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

ግለሰቦቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት የተጠረጠሩበት ወንጀል የእያንዳንንዱን ተሳትፎ የሚያሳዩ “ደላሎች” ተብለው የተገለፁት ሁሉም ደላሎች አለመሆናቸው፤ ነጋዴና የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ከመንግስት ወስደው የሚሠሩ ኮንትራክተሮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ፖሊስ ምርመራውን መቀጠል እንደሚችል እና ደንበኞቻቸውም በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ÷ አብዛኛዎቹ ተጠርጣሪዎች በሕገ ወጥ የመሬት ድለላ ሥራ ላይ መሰማራታቸውንና ገሚሶቹም የድለላ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ከፌዴራልና ክልል ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር በአዲስ አበባ የመሬት ወራራ እንደፈፀሙ እና በርካታ የሚጣሩ ጉዳዮች እንዳሉ አንስቷል።

ሐሰተኛ የአርሶ አደር እና የአርሶ አደር ልጆች ናቸው ብለው በማጻፍ ከክፍለ ከተማ እና ወረዳ የስራ ኃላፊዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ነዋሪ ያልሆኑትን ነዋሪ አድርገው መታወቂያ እስከ ማስወጣት ድረስ የሚያያስፈፀሙ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህም አመራሮች በራሳቸው ስም ንብረት የማያስመዘግቡ በመሆኑ ደላሎቹ ሽፋን በመስጠት በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ንብረትና ሃብት በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም መሰብሰባቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ከተጠበቀ በምስክሮች ላይ ጫና በመፍጠር ሊያሸሹ ስለሚችሉ፣ ከአመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የጥቅም ግንኙነት ስላለ የሰነዶችን ማረጋገጫ የሽያጭ፣ ወኪልና ሠነዶችንና ከተለያዩ ባንኮች ማስረጃዎችን እንዳይሰውሩና እንዳያጠፋ የተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት እንዳይፈቃድ ፖሊስ ጠይቋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman