የሰላም ስምምነቱ ውጤት የታለ?



በህወሃትና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያና በኬንያ ናይሮቢ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ውጤት እስከ አሁን አልታየም
የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ ነዋሪዎች በማቅረብ ላይ ካለው የሰብአዊ ድጋፍና የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ውጭ በተጨባጭ ይህ ነው የሚባል ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት እንዳልሆነ ይታወቃል
በተለይም ከፕሪቶሪያና ናይሮቢ የሰላም ስምምነት በኋላ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በሽሬ ከተወያዩ ወዲህ የትግራይ ታጣቂዎች በስምምነቱ መሰረት ትጥቅ ይፈታሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ቢጠበቅም በዚህ ረገድ በተጨባጭ የታየ ነገር የለም
በእርግጥ ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ ለትግራይ ሚዲያ በሰጡት መግለጫ 65 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ታጣቂ በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጓል፤ የሚቀረውም በጥቂት ቀናት ውስጥ ትጥቁን በመፍታት ወደተመደበለት ቦታ ይገባል በማለት በይፋ ቢናገሩም በተግባር ለህዝብ ይፋ የተደረገ ነገር አልታየም
የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይ ነዋሪዎች ከአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እንዲወጡ እያደረገ ያለው ጥረት በሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፤የኤሌክትሪክ አገልግሎትና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ እየተገለፀ ነው
የትግራይ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን መንግስት የሚታይ ጥረት በመዘገብ ረገድ ክፍተት አለባቸው፤ ሆን ተብሎ የሚደረግ መሆኑም ይታወቃል
ለምሳሌ "የትግራይ ነዋሪዎች የሰብአዊ ድጋፍ ቢቀርብልንም የኤርትራ ወታደሮች ከክልላችን ስላልወጡ ደስታችን የተሟላ አይደለም"ብለዋል ዓይነት ዘገባ ለምን እንደሚሰራ ይታወቃል
ህብረተሰቡ በጦርነቱ ምክንያት ያጣቸውን አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኝ ከማበረታታት ይልቅ ቀዳዳዎችን የመፈለግ አዝማሚያ በተጨባጭ እየታየ ነው እንግዲህ'የዘፈን ዳር ዳሩ እስክስታ ነው"እንዲሉ በህወሃት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሚዲያዎች በዚህ ዓይነት ሁኔታ በመዘገብ ላይ የሚገኙት ለምን ይሆን በማለት መጠርጠር ይቻላል
በፊንፊኔ/አዲስ አበባ በማይገባ ምክንያት የተጀመረው እሰጥ አገባም ለህወሃት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ይመስላል
አሁን ባለው ሁኔታ ህወሃት ለአራተኛ ዙር ወረራ እየተዘጋጀ ሊሆን ይችላል ብሎ መጠርጠር ተገቢ ይሆናል
በሌላ በኩል ቀደም ሲል ለህወሃት ቁንጮዎች መግለጫዎችን በመስጠትድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ጆሴፍ ቦሬል የሚባሉ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣን በጦርነቱ ምክንያት 8 መቶ ሺህ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች መሞታቸውን ነግረውናል፤ሰውዬው ይህን እንዴት ማወቅ ቻሉ? ማንስ ቆጠረላቸው?
ለማንኛውም የሰላም ምምነቱ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ሆኖ በጦርነቱ ምክንያት ለእንግልት ኑሮ የተጋለጠው ሕዝብ እፎይታ እንዲያገኝና ቀጣይ ኑሮውን መጠቀል እንዲችል ማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ግዴታና ኃላፊነት ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman