የአዲስ አበባ ፖሊስ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦችን አስጠነቀቀ

 




አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦችን አስጠነቀቀ።

ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ትናንት  ታህሳስ 4 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ተግባር በሰላም ሲካሄድ መዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ በመግለጫው ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦች " አጥፊ " ሲል ከጠራው ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የረብሻ እና የጥፋት ብሎም የውድመት መድረክ ለማድረገው በታቀደ ህገወጥ ተግባር ላይ አንዳንድ የባልደራስ ለእውነተኛዲሞክራሲ አባላት ቀጥታኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በማስረጃ  እንደተረጋገጠ ገልጿል።

በጥፋት ድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሣትፎ የነበራቸው አንዳንድ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነው  ችግሩን በማቀጣጠል እና ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሰብረው በመግባት በትምህርት ቤት ሀብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ያደረጉ የጥፋት አጀንዳ የተቀበሉ ሌሎች ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ብሏል።

" የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በማረገገጥ የከተማዋን ፀጥታ የማስጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎብኛል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ገልጾ ይህን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

የተማሪ ቤተሠቦችና ህብረተሰቡ እውነታውን በመረዳት ልጆቹን በመምከር ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

Ministiroota Itiyoophiyaa har'a muudaman

Ibsa Dhaabbatummaa Dh.D.U.O

Obbo Muktaar Kadir pireezidaantii Mootummaa Naannoo Oromiyaa ta’uun lammata filataman